2009-07-17 13:06:51

ሕፃን ወታደሮች


የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታና የደህንነት ምክር ቤት የሲሪላካ መንግሥት የአገሪቱ ታይገርስ በመባል የሚጠራው ያማጽያን ኃይል በውትድርናው ዓለም ያሳትፋቸው ለነበሩት ሕፃናት ሰብአዊ ስነ አእምሮአዊ RealAudioMP3 ድጋፍና ተሓድሶ በማቅረብ ከኅብረተሰብ ጋር በሰላም ተቀላቅለው ለመኖር የሚያስችላቸው እድል እንዲፈጥርላቸው መጠየቁ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

እነዚህ ሕፃናትን ለመደገፍ በቅድሚያ የሚሰለፉት የተለያዩ የግብረ ሰናይ ማኅበራት ስሪላንካ ለመግባት ፍቃዱን እንዲሰጣቸው የዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን ፊርማ የሰፈረበት የምክር ቤቱ መልእክት እንደሚያመለክተው ሲር የዜና አገልግሎቱ አስታውቆ፣ ህጻናቱን በውትድርናው ዓለም የከተተ ለይቶ ለህግ ለማቅረብ እንዲቻልም ተገቢ መረጃ ለማሰባሰብ የአገሪቱ መንግሥት ጥብቅ ክትትልና ምርመራ ያደርግ ዘንድ ባን ኪ ሙን ጠይቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.