2009-07-17 13:02:53

ሕንድ እና ፓኪስታን በጋራ አሸባሪዎችን ለማጥፋት


አሸባሪዎችን ለማጥፋት ሕንድ እና ፓኪስታን የጋራ ጸረ አሸባሪያን ትግል ሊያካሂዱ መሆናቸው በግብጽ ሻርም ኤል ሼክ በመካሄድ ላይ ባለው የገለልተኛ አገሮች ማኅበር ጉባኤ ተገኝተው ከዚሁ ጉባኤ ውጭ RealAudioMP3 ሁለቱ አገሮች ባካሄዱት የጋራ ግኑኝነት መስማማታቸው ተገለጠ።

ይህ በንዲህ እንዳለም በፓኪስታን ያልቃይዳ ደጋፍያን አክራሪዎች በሚፈጽሙት የሽበራ ተግባር አገሪቱ ለማኅበራዊና ሰብአዊ ውጥረት እየዳረጉ መሆናቸው በቅርቡ እነዚህ አክራሪያን አንድ በአገሪቱ የተባበሩት መንግሥታት ሠራተኛ ላይ የፈጸሙት የቅትለት ተግባር ይመስከረዋል።

የኤኮኖሚ ሊቅ የዓለም አቀፍ ያሸባሪያን ጉዳይ ጠንቀቀው የሚያውቁ ሎሬታ ናፖለኦኔ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ፓኪስታን በጸረ ታሊባንና አልቃይዳ ትግል ከተሰለፉት አገሮች ውስጥ ነች፣ በአገሪቱ ያለው ማኅበራዊ ፖለቲካዊ ውጥረት ለማርገብ ፖለቲካዊ ፍላጎቱ አለ፣ በጠቅላላ በአገሪቱ ጸረ አሸባሪያን ትግል እየተካሄደ ቢሆንም ቅሉ ዓላማው ግቡን ይመታል ብየ ለመናገር ግን አልደፍርም” ብለዋል። አክለውም ስለ አፍጋኒስታን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ “ባፍጋኒስታ በኢሳፍ እየተመራ ያለው የጸረ አሸባሪያን ትግል አመርቂ ውጤት እያስገኘ ነው ብሎ ለመናገር ያዳግታል፣ ይህ ደግሞ በስዋት ሸለቆ የመሸገው የታሌባን ኃይል ለማጥፋት ክልሉን ለመቆጣጠር እየተካሄደ ያለው ጸረ አሸባሪያን ትግል የሚመሰክረው ነው” ብለዋል።

የታሌባን ሃይሎች የተሟላ የጦር መሣሪያ እንዳላቸውና የመሸጉበት ክልል ጠንቅቀው የሚያውቁ መሆናቸው የሚያረጋገጥ ብቻ ሳይሆን እንደሚታወቀውም በዚህ ክልል ማንም የውጭ ኃይል የተነሳበት ዓላማ ግቡን ኣላስመታም”፣ ካሉ በኋላ “በቅርቡ ባገሪቱ ይካሄዳል የሚባለው ሕዝባዊ ምርጫ በአገሪቱ ያለው ሁኔታ ይለውጠዋል የሚል ግምት የለኝም፣ ምክንያቱም ባፍጋኒስታን የነበረው የታሌባኑ መንግሥት መውደቅ ወዲያውኑ ብዙ ባድናቆት የተለፈፈው የዴሞክራሲው ሥርዓት ውጤት እያስገኘ አለ መሆኑና፣ ይህ ደግሞ ዴሞክራሲያዊው መንግሥት መላ የአገሪቱ ክልል ለማስተዳደር ለመቆጣጠር ካልቻለ በአገሪቱ ያለው የዴሞክራሲው ሥርዓት እምብዛም ተሰሚነት እንደሌለው ነው የሚያረጋገጥልን” ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.