2009-07-16 08:41:06

“የምርምር ጉዞ ለመናብረተ ጥበባት የባህል እድገት”


የሮማ ሰበካ የትምህርት ቤቶች እና የመናብርተ ጥበባት ሓዋርያዊ ኖልዎ የሚንከባከበው ድርገት ፍቅር በሓቅ የተሰኘችው በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ የተደረሰቸው አዋዲት መልእክት ማእከል ያደረገ የኤኮኖሚ ሊቃውንትና ምሁራንን የጠራው ዓውደ ጥናት እየቀጠለ ነው።

ይህ “የምርምር ጉዞ ለመናብረተ ጥበባት የባህል RealAudioMP3 እድገት” በሚል ርእስ ሥር የተመራ ዓውደ ጥናት መሆኑም ተገልጠዋል።

ዓውደ ጥናቱን በንግግር የከፈቱት ጳጳሳዊ የፍትህና ሰላም ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ሬናቶ ራፋኤለ ማርቲኖ መሆናቸው ሲነገር፣ ብፁእነታቸው ባሰሙት ንግግር ለጋር ጥቅም ያቀና የተሟላ እድገት ለማረጋገጥ የሚያስችል ር.ሊ.ጳ. ኤኮኖሚ መሠረት ያደረገ ያመለከቱት መንገድ ሰፊ በማድረግ አብራርተዋል።

ሮማ በሚገኘው ቶር ቨርጋታ መንበረ ጥበበ የስነ ኤኮኖሚ መምህር የኤኮኖሚ ሊቅ ለዮናርዶ በከቲ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ “ኤኮኖሚ ሰውን በሙላት ማእከል ያደረገ የተወሳሰበው የሰው ልጅ ሁኔታ እግምት ውስጥ ያስገባ፣ በሰው ልጅ መካከል ያለው የአብሮ የመኖር እንዱ ካንዱ ጋር ያለውን የመገናኘት ባህርይ እግምት ውስጥ ያስገባ፣ መተማመን ተካፍሎ መኖር የሚሉትን ዕሴቶች የሚከተል መሆን እንዳለበት እና ይኸንን መንገድ የሚከተል ኤኮኖሚ ፍሬአማ እንደሚሆን አያጠራጥርም” ብለዋል። “ኤኮኖሚ የገዛ እራሱ የግብረ ገብና ሥነ ምግባር መመዘኛ ሊኖረው ይገባል፣ እንጂ ቅጥ የሌለው ከሕግና ሥርዓት በላይ መሆን የለበትም” ብለዋል።

“ስለዚህ ነጻነት በኃላፊነት መመራት እንዳለበት እና የማህብራዊ ሕግ ወንድማማችነት ትብብር እና መቋደስ የተሰኙት እሰይቶች መሆን እንዳለበት በስፋት የተብራራባት ዓዋዲት መልእክት ነች” ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.