Home Archivio
2009-07-16 08:42:41
ኩባ
በኩባ የሬግላ ማሪያማዊ ቅዱስ ሥፍራ እ.ኤ.አ. ከ 1997 ዓ.ም. አስተዳዳሪ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት 74 ዓመት ዕድሜ የነበራቸው አባ አሮዮ መሪኖ ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸው የኩባ ቤተ ክርስትያን የተላለፈ ዜና አስታውቀዋል።
የኩባ ብፁዓን ጳጳስት ጉባኤ ቃል አቀባይ የሰጡትን መግለጫ ኣባ መሪኖ ለእረፍት ወደ ስፐይን ለመሄድ በመዘጋጀት ላይ እንደነበሩ ሲያስታውቅ፣ የኩባ ሕዝብ ያለው የሃይማኖት ባህል እግምት ውስጥ ያስገባ፣ ሓዋርያዊ ኖልዎ በመከተል ይሰጡት በነበረ መንፈሳዊ ማኅበራዊ እና ሰብአዊ አገልግሎት በምእመናን እና በሕዝብ ዘንድ እጅግ እተወደዱ እንደነበርም ቃለ አቀባዩ የሰጡት መግለጫ ይጠቁማል።
ይህ በንዲህ እንዳለ ባለፈው የካቲት ወር ኣባ ደ ላ ፉወንተ በኩባ ርእሰ ከተማ መገደላቸው የሚዘከር ሲሆን፣ ሁለቱ ካህናት የስፐይን ዜጎች መሆናቸውም የኩባ ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ ቃል አቀባይ ኤሊዛርዶ ሳንቸስ መግለጣቸው ያሳወቀው አንሳ የዜና አገልግሎት በማሳወቅ ሁለት ሰዎች የአባ ደ ላ ፉወንት ቅትለት ተጠያቂ ናቸው በሚል ጥርጠራም ለምርመራ በቁጥጥር ሥር ማዋላቸው የዜና ምንጩ አክሎ አስታውቀዋል።
All the contents on this site are copyrighted ©.