2009-07-16 08:36:59

በኢራቅ አብያተ ክርስትያናት የቦምብ ጥቃት ተፈጸመ


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በቅርቡ በኢራቅ ክርስትያን የአምልኮ ሥፍራዎች ላይ የተፈጸመው የጥቃት ተግባር በእጅጉ እንደሚሳዝናቸው ገልጠው፣ ይህ ዓይነቱ የአመጽ ተግባር በአስቸኳይ እንዲቆም RealAudioMP3 የኢራቅ መንግሥት ባለ ሥልጣናትን በአጽንኦት አሳሰቡ።

የአመጹ ተግባር ሆን ብሎ የተደረገ ወንጀል እንዳይሆን ይገመታል። ቅዱስነታቸው በቅ. መንበሩ ዋና ጸሓፊ በብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ በኩል ወደ ከለዳዊት ባቢሎን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አማኑኤል ደሊ ሦስተኛ በላኩዋት መልእክት የአመጹ ጠንሳሾች ልብ እንዲለወጥ ጸሎት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ገልጠው፣ በመንፈስ ከኢራቁ ካቶሊካዊ እና ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረ-ሰብ ጎን መቆማቸውን አረጋግጠዋል።

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በመልእክታቸው የኢራቅ መንግሥት ባለሥልጣናት ለሁሉም የኢራቅ ዜጎች አብሮ ተቻችሎ በሰላም መኖርን እና ፍትሕን እንዲያሰፍኑ የተቻላቸውን ሁሉ እንዲጥሩ መክረዋቸዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.