2009-07-16 08:39:25

ሆንዱራስ


በሆንዱራስ የአገሪቱ ወታደራዊ ኃይል ስኔ 28 ቀን 2009 ዓ.ም. በፈጸሙት የመንግሥት ግልበጣ ሴራ የተከሰተው መንግሥታዊ ቀውስ እና ውጥረት ሻል እያለ መምጣቱ ይነገራል። በተካሄደው የመንግሥት ግልበጣ ሴራ ከስልጣናቸው የተነሱት በኒካራጉዋይ በስደት ላይ የሚገኙት ርእሰ ብሔር ማኑኤል ዘላያ ወደ አገራቸው ለመመለስ ያላቸውን ፍላጎት እንዳላመከኑ ይነገራል። RealAudioMP3 የኮስታ ሪካ ርእሰ ብሔር የሰላም ኖቤል ተሸላሚ ኦስካር አሪያስ በተባበሩት መንግሥታት ፍላጎት መሠረት የሆንዱራስ የመንግሥት ቀውስ ሰላማዊ መፍትሔ ያገኝ ዘንድ እያካሄዱት ላለው ጥረት ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን ሙያዊ ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸው አስታውቀዋል።

በተፈጸመው የመግንሥት ግልበጣ ሳቢያ ሥልጣናቸው ለቀው ለመሰደድ የተገደዱት ርእሰ ብሔር ማኑኤል ዘላያን በሚደግፉ እና ጊዚያዊው ያገሪቱን መንግሥት በሚደገፉት መካከል የተፈጠረው ውጥረት ወደ ከፋው ያገር ውስጥ ግጭት እንዳያዘግም ያሰጋል። ባገሪቱ ርእሰ ከተማ ተጉቺጋልፓ የሚገኘው መንበረ ጳጳስ የሆነው ካቴድራል ለሦስተኛ ጊዜ የጥቃት ኢላማ መሆኑ ሲገለጥ በሌሎች ሦስት አቢያተ ክርስትያናት የጥቃት ዛቻ በመተላለፉ ምክንያት ባለፈው እሁድ ቅዳሴ ለማቅረብ አለ መቻሉ ተገልጠዋል።

ባለፈው እሁድ ቅዱስ አብታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በሆንዱራስ ተከስቶ ያለው ፖለቲካዊ እና ማኅብራዊ ወጥረት እንዲወገድ፣ ሁሉም ምእመናን ለዚህች አገር ሰላም ይጸልይ ዘንድ የውጥረቱ ዋና ተዋናያን የፖለቲካ አካልት ለውይይት እና ለዕርቅ ያተኵሩ ዘንድ ጥሪ ማስተላለፋቸው የሚዘከር ነው። በአገሪቱ ስላለው ወቅታዊው ሁኔታ በማስመልከት የሆንዱራስ ርእሰ ከተማ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ኦስካር አንድረስ ሮድሪግዝ ማራዲያጋ ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ “ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የሆንዱራስ ፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ ውጥረት ይወገድ ዘንድ ያስተላለፉት ጥሪ ለብቻችን እንዳልሆን የሚያረጋገጥልን” ነው ካሉ በኋላ “ቤተ ክርስትያን ለማንም ወገን እታደላም እርቅ ሰላም እንዲረጋገጥ ችግር በውይይት እንዲቀረፍ አደራ ትላለች፣ ስለዚህ የሆንዱራስ ቤተክርስትያን በአሁኑ ወቅት በበለጥ ወንጌልን መከተል እንደሚያሻ የሚያሳስብ ሁኔታ ነው። የተፖለቲካ ሠልፎች የአገርና ህዝብ ጥቅም መሠረት በማድረግ የተለያየ ሐሳብ እና አመለካከት ሊኖራቸው ይችላል፣ ሕግን ለመጣስ አንዱ የፖለቲካ ሠልፍ የእራሱን አመለካከት ሌላው ባስገዳጅ እንዲስማመበት እንዲቀበለው ኃይል መጠቀም ወንጀል ነው። የእርስ በእርስ ጥላቻና የቂም በቀል ጥማት እንዲሁም አመጽን በማግለል በጋራ ያገሪቱ የመጪው እድል ብሩህ ይሆን ዘንድ ሁሉም መንገዱን እውነት ያደርግ አደራ” ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.