2009-07-13 13:59:55

“ፍቅር በሓቅ” የአባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ አስተንትኖ


RealAudioMP3 የቅድስት መንበር የዜናና የማህተም ክፍል ተጠሪ፣ የቫቲካን ረድዮ ጠቅላይ አስተዳድሪ ኣባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ፣ ቅዱስ አብታችን “ፍቅር በሓቅ” በሚል ርእስ ሥር የደረስዋት አዋዲት መልእክት በማስደገፍ በሰጡት የርእሰ አንቀጽ ዓምድ መግለጫ፣ አዋዲት መልእክት የፍቅር ሥራ በተመለከተ ምን መደረግ እንዳለበት ለሚለው ብቻ ሳይሆን ለምታንጸባርቀው የእምነት ጉዳይ ጭምር ግምት መስጠት ወሳኝ ነው ካልሆነ ግን የተሟላ ግንዛቤ ኣይኖርም” ብለዋል።

“የሰው ልጅ የነገውን ሕይወት ከወዲሁ ለማቀድ ኃይል አግኝቶ ለመገንባት በተሻሩት የተለያየ ርእዮተ ዓለም ድጋፍ ሳይሆን፣ በነጻነት ማለትም ከልምድ አንጻር የተገኙት አወንታዊ አሉታዊ ከእወቅት ዘርፎች ከድካምና ከምርምር የሚገኘው ልምድ ሁሉ እግምት ውስጥ በማስገባት የእምነት አስተንፍሶ ወሳኝ መሆኑ የምታስተምር ናት” ብለዋል።

ቅዱስ አባታች በአዋዲት መልእክት “የሰውን ልጅ ባስደናቂው የስጦታ ወይንም የጸጋ ልምድ ፊት የሚያቀርብ ገዛ ራሱ ‘ሰው ጸጋ ነው የሚለው ሓቅ ተገንዝቦ በዚህ አማካኝነትም በውስጡ ያለውን መልእልተ ባህርይ ይገልጣል እግብር ላይም ያውላል። ይህ ደግሞ የጸጋ ወይንም የስጦታ መሠረታዊ ሥነ አመክንዮ ነው። ስለዚህ የሰው ልጅ በተለያየ ዘርፉ ለስቃይ የሚዳርጉትን ችግሮች ለመቅረፍ ወንድማማችነት መሠረትና ቁልፍ መሆኑ እንዲገነዘብና ይህ ደግሞ በዓለማዊነት የትሥሥሩ ሂደት ጭምር ግምት ሊሰጠውና እግብር ላይ መዋል እንዳለበት ተብራርቶባት ይገኛል” ብለዋል።

የድኾች ስቃይና መከራ፣ የሌሎች ሃብታምነትና የበላይነት መግለጫ ሳይሆን የማኅህበረሰብ ኅሊና ማን መሆንህን ምን መሆንና እንዴት መሆን/መኖር እንዳለብህ የምታስተምር ከቁሳዊው ርእዮት መንጥቀን መሄድ እንዳለበ ታሳስበናለች፣ ስለዚህ ይኽ መሠረታዊ ሐሳብ ግምት ካልተሰጠው ዓለማዊነት ትሥሥር የሕይወት ዕድልና ጥሩ አጋጣሚ መሆኑ ቀርቶ በታሪክ ለሚዘከሩት ዓበይት ችግሮች እንደምንጋለጥ” የምታሳስብ መልእክት ነች ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.