2009-07-13 13:57:40

የኤውሮጳ የመናብረተ ጥበባት ተማሪዎች ጉባኤ


“ወቅታዊ የኤማኡስ ሓዋርያት፣ ክርስትያንነት በመንበረ ጥበባት” በሚል ርእስ ተሸኝቶ እዚህ ሮማ ሲካሄድ የሰነብተው የመላ ኤውሮጳ የመናብርተ ጥበባት ተማሪዎች ጉባኤ ባለፈው ቅዳሜ ተጋባእያኑ ከር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ጋር በመገናኘትና ከቅዱስነታቸው መሪ ቃል በመቀበል ተፈጽሟል።

በግኑኝነቱ ወቅት ቅዱስ አባታችን ያሰሙት ንግግር RealAudioMP3 “ጥሪ ክርስቶስን ለማወቅና ከርሱ ጋር ለመገናኘት የሚያበቃ የተሰኘ ሐሳብ ማእከል ያደረገ እንደነበርም ተገልጠዋል። በዚህ አንደኛው የኤውሮጳ የመናብርተ ጥበባት ተማሪዎች ጉባኤ፣ ከተለያዩ 31 የኤውሮጳ አገሮች የተወጣጡ ተማሪዎችን ያሳተፈ እንደነበርም ሲነገር፣ የኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤዎች ህብረት ሥር የሚመራው የኤውሮጳ የትምህርተ ክርስቶስ የትምህርት ቤቶችና የመናብረተ ጥበባት ሓዋርያዊ ኖልዎ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ድርገት ያነቃቃው ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለተጋብእያኑ ባሰሙት ንግግር “እናንተ ወጣቶች ስላላችሁ እምቁ ኃይል እና ኃላፊነት ጭምር ግንዛቤ ሊኖራችሁ ይገባል፣ ልክ ቅዱስ ቤነዲክቶስ ለኤውሮጳ የሰብአዊና የመንፈሳዊ ብሰልት ባህልዊ ዕድገት ወሳኝ መሆኑ እንደተገነዘበው ሁሉ፣ እናንተም በወንጌል ፍቅር ላይ የተገነባ ማህበረሰብ ግንባታ ዋና ተወናያን ሁኑ። ይከንን እውን ለማረግም የኤማኡስ ደቀ መዛሙርት የመንፈሳዊና የሰብአዊ ተጨባጭ አብነት በመከተል፣ ሞትን አሸንፎ የተነሳው ክርስቶስ በቤተክርስትያናችሁ ዘንድ በተለይ ደግሞ በቅዱስ ቅርባን በመሳትፍ የራስችሁ ተመክሮ ማድረግ ይኖርባችኋል” ብለዋል።

“የመናብርተ ጥበባት ጥሪ እዕምኖርን ማሰልጠን ነው፣ የእውቀት ዘርፍ ተወሳሳቢነትና እጅግ ሰፊ በመሆኑም ጭምር በግብረ ገብ እና በመንፈሳዊነት ጥራት መደገፍ ይኖርበታል። ምክንያቱም ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገርና ለመወያየት ብቃት ያላቸው ምሁራን ያስፈልጋሉና” ብለዋል። “የመናብርተ ጥበባት ሓዋርያዊ ኖልዎ ጉዳይ የሚከታተሉት ሁሉ ያለውን ቲዮሎጊያዊ እና መፍነሳዊው ኃላፊነት አጥብቆ የተረዳ፣ ወጣቶች ከክርስቶስ ጋር እንዲገናኙ እና ይኽ ግኑኝነት የሰው ልጅ እና የታሪክ ጥልቅ ሚሥጢሩን እንዲገነዘቡት የሚያበቃ ድጋፍ ሊያቅርብ ይገባል” ብለዋል።

“እምነት ለሰው ልጅ የማወቅ ፍላጎት ወደርና ምትክ የማይገኝለት አገልግሎት እንደሚሰጥ ከጥንት ጀምሮ የተረጋገጥ ሓቅ ነው፣ ስለዚህ ይህ ለዘመኑ ኅብረተሰብ የዕድገት መሠረት ነው። አንድ ህዝብ ሕልውናና ታሪክ በቁሳዊው ርእዮት መሠረት ብቻ ከማጤን የመነጨ ከሚያጋጥሙት እክሎች ባሻገር የነገውን ሕይወት በተስፋ ለመመልከት እንዲችል በእምነት የተደገፈ እውቀት ሊኖርረው ይገባል” ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.