2009-07-13 14:05:01

ኮንጎ ብራዛቪል


በኮንጎ ብራዛቪል የርእሰ ብሔርነት ተልእኳቸውን ያገባደዱት ርእሰ ብሔር ዴኒስ ሳሱ ንጉዌሶ ዳግም እጩ ተመራጭ ሆነው የቀረቡበት ሕዝባዊ ምርጫ ትላንትና ተካሂደዋል። እንደሚባለውም ከሆነ ርእሰ ብሔር ንጉዌሶ RealAudioMP3 የማሸነፍ እድል ያላቸው ይመስላል። ከአሥራ ሦስቱ እጩ ተመራጮች ውስጥ 6 ሕዝባዊው ምርጫው ከሥርዓት ውጭ ነው በማለት ክስ ሲያቀርብ ያገሪቱ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ማህበር እና የምርጫው ታዛቢ የኤውሮጳ ህብረት ልኡካን የመምረጥ መብት ያለው ሕዝብ በገፍ የተሳተፈበት ምርጫ ነው ተብሎ ባገሪቱ እየተሰጠ ያለው አኅዛዊ መግለጫ አጠያያቂ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.