2009-07-13 14:02:00

አንደኛው የኤውሮጳ ህብረት መናብረተ ጥበባት ጉባኤ


የኤውሮጳ የብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤዎች ኅብረት የትምህርት ቤቶች እና መናብረተ ጥበባት ሓዋርያዊ ኖልዎ የሚንከባከበው ድርገቱ ያነቃቃው ትላንትና የተፈጸመው አንደኛው የኤውሮጳ የመናብረተ ጥበባት ተማሪዎች ጉባኤ RealAudioMP3 “አዲስ የኤማኡስ ሓዋርያ፣ ክርስትያንነት በመንበረ ጥበባት” በሚል ርእስ ሥር ስለ ተካሄደው ጉባኤ በማስመልከት የኤውሮጳ የብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤዎች ኅብረት የትምህርት ቤቶች እና መናብረተ ጥበባት ሓዋርያዊ ኖልዎ የሚንከባከበው ድርገቱ ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ማረክ ያድራስዊስኪ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ “ከወንጌል ከባህል በተለይ ደግሞ ከወጣቱ ኅብረተሰብ ጋር መገናኘት ለቤተክርስትያን የነገው ሕይወት እጅግ ወሳኝ ነው። በኤውሮጳ በአሁኑ ወቅት እግዚአብሔር እንደሌለ እድርጎ ከማሰቡ ግፊት የሚንጸባረቅ ባህል እየተስፋፋና በዚሁ ዓይነት አመለካከት ላይ የተገነባ ሕይወት ጎልቶ ይታያል፣ ስለዚህ ይህ ዓይነቱ ባህል በሚታይበት ማኅበረሰብ የሚኖር ክርስትያን በሚኖርበት በሚሠራበት በተለያየ ዘርፍ ክርስትናውን እንዴት ባለ መልኩ መኖር ይገባዋል ለሚለው መሠረታዊ ጥያቄ የመናብረት ጥበባት ተማሪዎች በጋራ መልስ ለመስጠት ያሰባሰበ ጉባኤ ነበር” ብለዋል።

“በዛሬው ሕይወት አማካኝነት የነገው ሕይወት ተስፋ የሆነውን ክርስቶስ ጋር በመገናኘት ተስፋን ማግኘትና መመሥከር የሁሉም ክርስትያን ጥሪ ነው፣ ከርክርስቶስ ጋር መገናኘት ሁሉን ይለውጣል፣ ኤውሮጳ ቃል የነበረው ሥጋ ለብሶ የወረደው ኢየስስ ክርስቶስ መሠረት ያድረገ አዲስ ሰብአዊነት መረጋገጥ ይኖርበታል፣ ስለዚህ ይኸንን ቃል ሥጋ ለብሶ የወረደውን እግዚአብሔር መሠረት በማድረግ የሚኖር ሁሉ በተሰማራበት ዘርፍ በዕለታዊ ኑሮው ሊኖረውና ሊመሰክረው ይገባል፣ ከእየሱስ ክርስቶስ የመነጨ አዲስ ሰብአዊነት እንዲህ ባለ መልኩ ብቻ ነው የሚረጋገጠው” በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.