2009-07-13 14:03:27

ሶማሊያ


ሶማሊያ ርዕሰ-ከተማ ሞቃዲሾ ውስጥ በመንግሥቱ ወታደሮችና በዓማጺያን መካከል እያየለ በሄደው ላይ ባለው ውጊያ 40 የአማጽያን አባላት መገደላቸው ይነገራል። የሶማሊያው የሽግግር መንግሥት ወታደሮች RealAudioMP3 ባፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል ተደግፎ በሰነዘረው የጥቃት ዘመቸው አማካኝነት በርእሰ ከተማይቱ ተወስኖ ከነበረበት የከተማዋ ክፍል ወጣ ብሎ ቁጥጥሩን እያስፋፋ ነው። የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስክባሪ ኃይል በሶማሊያ ሰላም ለማስከበር ከተሰማራበት ዕለት ጀምሮ በውጊያ ሲሳተም ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል።

ይህ ከባለፈው ወር ጀምሮ በሶማሊያ ያልቃይዳ የቀኝ እጅ ነው የሚባለው ያማጽያኑ ኃይል ጋር የተጀመረው ውግያ 350 ሰዎች ለሞት ሌሎች 1400 ለመቁሰል እና 200 ሺሕ የሚገመቱት ለመፈናቀል አደጋ መዳረጉ ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.