2009-07-11 08:20:39

ሶማሊያ


በሶማሊያ ያለው የሰብአዊ ችግር እጅግ ከቀን ወደ ቀን እየከፋ መምጣቱ ይነገራል። RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ከባለፈው ግንቦት 7 ቀን 2009 ዓ.ም. በአፍሪካ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ኃይሎች የሚደገፈው የአገሪቱ የመግንሥት ወታደሮች እና በሶማሊያ ላልቃይድ ቀኝ እጅ ተብሎ የሚነገርለ እስላማዊ አል ሻባብ እና ሂስብ ኡል ኢስላም መካከል የተቀጣጠለው መጠነ ሰፊ ግጭት ሕዝቡ ለሞት እና ለመፈናቀል እደጋ እያጋለጠ መሆኑ ፊደስ የዜና አገልግሎት ባስተላለፈው የዜና ምንጭ በመጥቀስ 200 ሺሕ የአገሪቱ ዜጎች ሞቃዲሾን ለቀው መውጣታቸውም አስታውቀዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞችና የተፈናቃዮች ጉዳይ የሚከታተለው የበላይ ድርገት እንዳመለከተውም በአሁኑ ወቅት በሶማሊያ እየታየ ያለው የሕዝቦች መፈናቀል አደጋ በጣም አሳሳቢ መሆኑና እየተካሄደ ባለው ጦርነት ሳቢያ ባለፈው ሳምንት ብቻ 105 ሰዎች መገደላቸውና 382 የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸውም አስታውቀዋል። የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞችና የተፈናቃዮች የበላይ ድርገት ቃለ አቀባይ እንዳሳወቁትም፣ በሶማሊያ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ብዛት 1,2 ሚሊዮን መድረሱንም አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.