2009-07-11 10:13:59

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የአውስትራልያ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የደቡብ ኮርያ ፕረሲዳንት ተቀብለው አነጋጋአሩ.


ቅዱስ አባታን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አሥራ ስድስተኛ ትናንትና ረፋድ ላይ የአውስትራልያ ጠቃልይ ሚኒስትር ሩድ እና የደቡብ ኮርያ ፕረሲዳንት ሊ ምዩንግ ባክ በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው በተናጠል ማነጋገራቸው የቫቲካን መግለጫ ያመልከታል።

በዚሁ መግለጫ መሠረት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ እና የአውስትራልያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሩድ በቅድስት መንበር እና የአውስትራልያ መንግስት መሀከል ያለውን ግኑኝነት እንዲሁም አለም አቀፍ ነክ ጉዳዮች በተመልከቱ ርእሰ ጉጋዮች ተወያይተዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ባለፈው ዓመት 2008 እኤአ ሐምለ ወር ላይ የወጣቶች ዕለት መሰረት በማድረግ ፡ በአውስትራልያ ባካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት የተደረገላቸውን መልካም አቀባበል በመንግስት እና ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን መካከል ያለውን ጥሩ ግንኙነት ማስታወሳቸው መግለጫው አስታወዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በተከታታይ የደቡብ ኮርያ ፕረሲዳንት ሊ ምዩንግ ባክ በጽሕፈት ቤታቸው እንደተቀበልዋቸው እና ከሳቸው ጋር የዓለም ኤኮኖምያዊ ቀውስ እና በታዳጊ ሀገራት ላይ ያለውን አንደምታ የደሴት ኮርያ ማሕበራዊ እና ፖሊቲካዊ ሁኔታ ትኩረት የሰጠ ውይይት ማካሄዳቸው የቫቲካን መግለጫ ለጥቆ አስገንዝበዋል።

በዚሁ መግለጫ መሠረት ፡ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ እና ፕረሲዳንት ሊ ምዩንግ ባክ በቅድስት መንበር እና በደቡባዊ ኮርያ መሀከል ያለውን ግኑኝነት በመንግስት እና ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን በዓውደ ትምህርት እና ማኅበራዊ ዘርፎች የሚያደርጉት ትግግዝ የውስጠ ሃይማኖቶች እና ውይይት በተመለከተ ሐሳብ ለሐሳብ ተለዋውጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.