2009-07-11 08:19:15

ህንድ፣ ኦሪሳ


የዛሬ አንድ ዓመት በፊት በህንድ ኦሪሳ ክልል አክራሪያን የሂንዱ ሃይማኖት ትከከታዮች ቀስቅሰዉት በነበረው ጸረ ክርስትያን ዓመጽ ምክንያት የተጎዱት ቤትንና ንብረታቸውን ያጡት ሁሉ ለመደገፍና የወደሙት አቢያተ ክርስትያናት RealAudioMP3 ቤተ ጸሎት እና የቤተክርስትያን ተቋሞች ዳግም ለመገንባት የኔው ደልሂ ማእከላዊ መንግሥት የድጋፍና የትብብር ወጪ እቅድ መመደቡ ተገልጠዋል።

የህንድ መንግሥት ይኽ ውሳኔ እውን ያደርግ ዘንድ የኦሪሳ ክርስትያኖች በተለያዩ መልኩ ጥሪ ሲያቀርቡ መቆየታቸውም የሚዘከር ሲሆን፣ የህንድ የጠቅላላ አቢያተ ክርስትያናት ምክር ቤት እና የህንድ ይሰብአዊ መብት ተሟጋች ማኅበር የሂንዱ አክራሪያን ምእመናን በሰነዘሩት ጸረ ክርስትያን አመጽ የደረሰው እልቂት በደል ያቢያተ ክርስትያናት መውደምና የክርስትያኖች መሰደድ የሚያወሳ ሰነድ እቅርበው እንደነበርም ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት ያሰራጨው የዜና ምንጭ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.