2009-07-08 15:14:30

የቡድን 8 ጉባኤ በጣልያን ተጀመረ፡


ዛሬ ከቀትር በኃላ በመሀከለኛው በጣልያን ላ’ኪላ ከተማ ላይ የG8 የቡድን ስምንት በኢንዱስሪ የበለጸጉ ሀገራት ጉባኤ ተጀምረዋል ።

ቡድን ስምንት ተብለው የሚጠሩ ሀገራት፡ ዩናይትድ ስቴትስ ካናዳ ብሪታንያ ጀርመን ጃፓን ኢጣልያ ፈረንሳ ሩስያ እና የኤውሮጳ ኅብረት መሆናቸው ይታወሳል።

በሌላ በኩልም በልማት ላይ የሚገኙ ታዳጊ በቡድን 5 የሚጠሩ ሀገራት ብራዚል ቺና ህንድ መክሲኮ እና ደቡብ አፍሪቃ ሲሆኑ የነዚህ ሀገራት መሪዎች በተናጠል እና ከቡድን ስምንትጋር በመቀላቀል ለመሰብሰብ እዚህ ጣልያን ውስጥ እንደሚገኙ ይታወቃል።

በነፓድ የሚታወቅ ለአፍሪቃ ልማት አዲስ አጋርነት የሚታወቅ ቡድን አባል ሀገራት እስፓኛ ቱርክ ነዘርላንድስ እና የሌሎች ሀገራት መሪዎች እዚህ ጣልያን ውስጥ በመገናኘት የአፍሪቃ ክፍለ ዓለም ወቅታዊ የኤኮኖሚ ሁኔታ እና የምግብ ዋስትና በተመለከተ ለመወያየት ነገ እንደሚሰበሰቡ ተመልክተዋል።

የቡድን ስምንት በኢንዱስትሪ የበለጸጉ ሀገራት መሪዎች የዓለም ኤኮኖምያዊ እና ፋይናንሳዊ ቀውሶች ዘላቂ መፍትሔ እንድያገኙለት የተለያዩ አገሮች አቀፍ ድርጅቶች እያሳሰቡ መሆናቸው ተነግረዋል ።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የዓለም ኤኮኖምያዊ ቀውስ ለመቅረፍ ጉባኤው በቡድን ስምንት ብቻ ሳይወሰን ታዳጊ ሀገራት እና አገሮች

አቀፍ ድርጅቶች ያሳተፈ እንዲሆን ለቡድኑ ግዝያዊ ሊቀመንበር ለጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ሲልቪዮ በርሉስኮኒ መልዕክት ማሰላለፋቸው ተነግረዋል።

የጣልያን መንግስት ያወጣው መግለጫ እንደሚያመለክተው ፡ ከቡድን ስምንት መሪዎች ሌላ የአርባ ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በዚሁ ዛሬ ከቀትር በኃላ የተጀመረው ጉባኤ ተሳታፊ ሁነዋል ።

ይህ በዚህ እንዳለ የዩናይትድ ስቴት መንግስት መሪ ፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ የቡድን ስምንት የመሪዎች ጉባኤ ከመጀመሩ በፊት ሩስያ ላይ የጀመሩት ጉብኝት ማጠቃለላቸው ከሞስኮ የደረሰ ዜና አስታውቀዋል።

ፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ ሞስኮ ላይ ከአቻቸው ከፕረሲዳንት ሴርጌይ መድቨደቭ እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ቭላዲሚር ፑቲን ጋር ያካሄዱት ውይይት ስኬታማ እና አዎንታዊ መኖሩ ይህ ከሞስኮ የደረሰ ዜና አስገንዝበዋል ።



ኢታር ታስ የሩስያ ዜና አገልግሎት እንዳመለክተው፡ የዩናይትድ ስቴትስ እና ሩስያ መሪዎች ኑክሌራዊ ጦር መሳርያ ለመቀነስ የስምምነት ፕሮቶኮል ተፈራርመዋል።

ፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ ሞስኮ ላይ አዲስ የኤኮኖሚ ከፍተኛ ትምህርት ቤት ተገኝተው ንግግር ማድረጋቸው በንግግራቸው ይዘታ ተደናቂነት ማትረፋቸው አብሮ የደረሰ ዜና አስታውቀዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት መሪ ፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ እና የሩስያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት የኢራን እና የሰሜን ኮርያ መንግስታት ኑክሌራዊ ጦር መሳርያ በተመለከተ የጆርጅያ እና ኡክራይን ሁኔታ ትኩረት በሰጠ ርእሰ ጉዳይ መወያየታቸውም አብሮ የደረሰ ዜና ገልጸዋል።

የ ዩ ኤስ አመሪካ መንግስት መሪ ፐሲዳንት ባራክ ኦባማ እና የሩስያው መሪ መድቨደቭ በቡድን ስምንት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ ትናንትና አምሻቸው ሮም ገብተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.