2009-07-08 13:08:50

ሰብአዊ ልክነት ያለው ዓለማዊ ትሥሥር


ቅዱስ አባታች ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ “ካሪታስ ኢን ቨሪታተ - ፍቅር በሓቅ” በሚል ርዕስ ሥር የደረስዋት ዓዋዲት መልእክት ትላንትና የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ዋና ኃላፊ ኣባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ አቀናባባሪነት RealAudioMP3 በዚህ የዜናና የማኅተም ክፍል አዳራሽ ጳጳሳዊ የፍትሕና ሰላም ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ረናቶ ራፋኤለ ማርቲኖ የዚህ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሃፊ ብጹዕ አቡነ ጃንፓውሎ ክረፓልዲ፣ የውሁድ ልብ ማኅበር ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፓውል ጆሴፍ ኮርደስ እና በኢጣሊያ ቦሎኛ ከተማ በሚገኘው መንበረ ጥበብ የስነ ኤኮኖሚ መምህር የኤኮኖሚ ሊቅ ስቴፋኖ ዛማኚ መግለጫ ሰጥተውበት በይፋ ለንባብ ቀርበዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ረናቶ ራፋኤለ ማርቲኖ ባሰሙት ንግግር “የአለማዊነት ትሥሥር ክስተት ለማስተዳድር ብቃት ያለው ሰውን ማዕከል ያደረገ እቅድ የሚረጋገጥበት ግዜ አሁን መሆኑ” ጠቅሰው፣ “ይኸንን ለመፈጸም የሚያግደውን እክል ሁሉ ለመቅረፍ፣ የሰው ልጅ እውነተኛ ማስፈጸሚያ ዘዴና ሃብት እንዲሁም መልካም ፈቃድ መሠረት በማድረግ እንዲሠራ የሚያሳስብ እና ይኸንን ለማረጋገጥ ምን መደረግ እንዳለበት የምትመራ ዓዋዲት መልዕክት ነች” ብለዋል። ብፁዕ ካርዲናል ፖውል ጆሴፍ ኮርደስ በበኩላቸውም “ሕዝባዊ ዕድገት - ፖፖሎሩም ፕሮግረሲዮ የተሰኘቸው በር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ እ.ኤ.አ. መጋቢት 23 ቀን 1967 ዓ.ም. የተደረሰችውን ዓዋዲት መልእክት ፈር በመከተል ቤተክርስትያን ዕድገት እንዳይረጋገጥ የሚደነቅኑት ችግሮች ለመቅረፍ ቴክኒካዊ መፍትሔ የላትም፣ የመንግሥታት እና የፖለቲካውን ዓለም ለመተካት አትቋምትም፣ ይኽ ደግሞ የቤተክርስትያን የማኅበራዊ ትምህርት የተስተካከለ ፍጹም ማኅበረሰብ ለማጋገጥ የሚያግዝ ሶስተኛ አማራጭ መንገድ የሆነ የፖለቲካ መርሃ ግብር አይደለም” ብለዋል። በመቀጠልም ብፁዕ ኣቡነ ጃንፓውሎ ክረፓልዲ፣ “የቤተክርስትያን የማኅበራዊ መሪ ትምህርት የግብረ ተልእኮ መሣሪያ ነው” በማለት “ሰውን በማህበራዊ ኑሮው ብቻ የሚገለጥ እንዳልሆነ የሚያስረዳና አለ እግዚአብሔር ዕድገት ለማረጋገጥ እንደማይቻል፣ ይኽም ስነ ምግባር መሠረት ሳይደረግ የማኅበራዊ ጉዳይ ጥያቄዎች ለመፍታት እንደማይቻል የሚያስተምር ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.