2009-07-08 15:01:20

ርአሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የጃፓን መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ታሮ አሶ ተቀብለው አነጋገሩ፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ሥድስተኛ ትናንትና ረፋድ ላይ የጃፓን መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ታሮ አሶ ከባለ ቤታቸው እና ተከታዮቻቸው በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸው ከቫቲካን የወጣ መግለጫ አስታውቀዋል ።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ እና የጃፓን መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ታሮ አሶ በቅድስት መንበር እና በጃፓን መሀከል ያለውን ግንኙነት ዓለም አቀፍ የኤኮኖሚ ቀውስ እና የአፍሪቃ ኤኮኖሚ ሁኔታ እና ርዳታ ትኩረት በሰጡ ርእሰ ጉዳዮች መወያየታቸው መግለጨው አብራርተዋል።

የጃፓን መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ታሮ አሶ ከየቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ከብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ እና በቅድስት መንበር የውጭ ጉዳይ ዋና ሐላፊ ከሊቀጳጳስ ከብፁዕ አቡነ ዶመኒክ ማምበርቲ ጋር ተገናኝተው በተመሳሳይ መወያየታቸው መግለጫው አመልክተዋል።

በቅድስት መንበር እና በጃፓን መንግስት መሀከል መልካም ግንኙነት መኖሩ መግለጫው በተጨማሪ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.