2009-07-08 13:16:46

ሆንዱራስ


በሆዱራስ የመከላከያ ኃይል በተደገፈ ሴራ አማካኝነት የተገለበጠው በዲሞክራሲው ደንብ አማካኝነት ኃላፊነቱን የጨበጠው በማኑኤል ዘላያ የሚመራው የአገሪቱ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ዳግም ሥልጣኑን ይረከብ ዘንድ RealAudioMP3 የተባበሩት ያሜሪካ መንግሥት ርእሰ ብሔር ባራክ ኦባማ ትላትና በሞስኮ በሚገኘውው የስነ ኤኮኖሚ መንበረ ጥበብ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር ጠይቀዋል።

ርእሰ ብሔር ኦባማ አክለውም ሕዝቦች የሚበጃቸውን ይመራኛል የሚላቸውን ያመራር አካላት የመምረጥ ነጻነቱ መከበር ይኖርበታል ብለዋል።

በስደት የሚገኙት የተገለበጠው መንግሥት መሪ ርእሰ ብሔር ማኑኤል ዘላያ ከትላትና በስትያ ባገራቸው የተከስተው ፖለቲካዊ ማኅበራዊ ውጥረት መፍትሔ ለማፈላለግ ከተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት ዋና ጸሓፊ ሂላርይ ክሊንተ ጋር በዋሽንግተን መገናኘታቸው ተገልጠዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም በአገሪቱ ተከስቶ ያለው ሁከት ለማስወገድ የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ የአገርና የሕዝብ ጥቅም ያስቀደመ መፍትሔ ወሳኝ ነው እንዳለም ለማወቅ ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.