2009-07-03 17:41:38

የካቶሊካውያን ማኅበራት ለቡድን ስምንት ሐሳብ አቀረቡ ፡


ፊታችን ሳምንት ሐምለ ስምንት ቀን እዚህ ጣልያን ሀገር ውስጥ ላ’ኲላ ከተማ የቡድን ስምንት በኢንዱስትሪ የበለጸጉ ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ እንዲከናወን በእቅድ መያዙ የሚታወስ ነው።

የቡድን ስምንት መሪዎች ፡ የተስፋ አጀንዳ በማዘጋጀት በተለይ የአለም ወጣቶችን ሁነኛ ተስፋ የሚሰጥ አዎንታዊ ርምጃ ይወስዱ ዘንዳ የሚያሳስብ መልዕክት ማዘጋጀታቸው የካቶሊካውያን ማኅበር አስታወቀ።

የካቶሊካውያን ማኅበሮች አንድነት መግለጫ እንዳስታወቀው ፡ የቡድን ስምንት መሪዎች ዓለም አቀፉ የኤኮኖሚ ቀውስ የሚቀርፍ ተጨባጭ ርምጃ እንዲወዱ እና ቀውሱ በአለም ህዝቦች ላይ እያወረደ ያለው ዓቢይ ችግር ለመግታት ዝግጁ መሆን ይጠበቅባቸውል ።

የጣልያን የካቶሊካውያን ማኅበሮች አንድነት ፡ በኢንዱስትሪ የበለጸጉ ሀገራት መሪዎች የተስፋ አጀንዳ አውጥተው ሁነኛ አዎንታዊ ድርጊት እንዲፈጽሙ የሚያሳስብ መልዕክት በማዘጋጀት በጳጳሳት የተመራ የልዑካን ቡድን ለጣልያን የፋይናንስ የውጭ ጉዳይ እና የማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሮች እንደሚያስረክቡ መደረጉ ተያይዞ ተመልክተዋል።

የጣልያን ካቶሊካውያን ማኅበራት አንድነት ዋና ጸሐፊ ሰርጅዮ ማረሊ እንደገለጡት፡ በኢንዱስትሪ የበለጸጉ ሀገራት የኤኮኖሚ ቀውስ አሳብበው ለድሀ ሀገራት የሚሰጡት የልማት ርዳታ እንዳይገቱት ዓቢይ ስጋት አለ።



የኤኮኖሚ ቀውሱ ከተከሰተ ወዲህ ፡በኢንዱስትሪ የበለጠጉ ሀገራት ቀውሱን ለመግታት እና ስራ አጥ እየሆነ የመጣውን ህዝብ ሁኔታ በተመለከተ ፡ በጋራም ሆነ በተናጠል ተጨባጭ ርምጃ ሲወስዱ አለመታየታቸውም አሳሳቢ መሆኑ ሰርጅዮ ማረሊ ገልጠዋል።

ሌላ ግራ አጋቢ እና ለመረዳት አቸጋሪ ያሉት ፡ ኤኮኖሚ ቀውሱ ፡ ዓለም አቀፍ ሆኖ እያለ በኢንዱስትሪ የበለጸጉ ሀገራት ታዳጊ ሀገራትን ወደ ጐን በመተው ፡ ለብቻቸው መፍትሔ ማፈላለግ መፈለጋቸው ነው።

ዓለም አቀፍ የኤኮኖሚ ቀውሱ ለመቅረፍ ሲፈለግም ሰው ማዕከል ያደረገ መፍትሔ እንዲሆን እንፈልጋለን ያሉት ሰርጅዮ ማረሊ ለቡድን ስምንት የተላከወን መልዕክትም ይህን የሚያመለክት መሆኑ ገልጠዋል።

ዓለም አቀፍ የኤኮኖሚ እና የፋይናንስ ቀውሱ በሚልዮን የሚቆጠር ህዝብ እየተፈታተነ መሆኑም ማረሊ በተጨማሪ አመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.