2009-07-03 17:50:02

የሰማዕታት ዘመን


“የሰማዕታት ዘመን፣ እ.ኤ.አ የ 900 ዎች ዓመተ ምሕረት ክርትያኖች” በተሰኘው ርእስ ሥር ባለፉት የ 900 ዓመታት እና በዚህ ባለንበት ዘመን የክርስትያኖች የደም ሰማዕትነት ጉዳይ የሚመለከት በቅዱስ ኤጂዲዮ የሚጠራው የካቶሊክ ማኅበረ-ሰብ መሥራች ፕሮፈሶር የታሪክ ሊቅ አንድረያ ሪካርዲ ያቀረቡት ልዩ የጥናት ሰነድ ከትላንትና በስትያ እዚህ ሮማ በሚገኘው በቲበሪያደ ደሴት ባለው የቅዱስ በርጠለሚዮስ ባሲሊካ በይፋ መቅረቡ ተገለጠ።

ክርስትያን ሰማዕታት በምስክረት፣ የክፋትን መንፈስ ለመቋቋማን ለመገሰጽ የከፈሉት የደም ሰማዕትነት፣ ስለ ክፋት እና አመጽ በተመለከተ ጉዳይ ዳግም ወይይትና ጥናት እንዲካሄድ የቀሰቀሰ አጋጣሚ መሆኑ ተገልጠዋል።

በተካሄደው ዓውደ ጥናት ፕሮፈስሮ ሪካርዲ ባሰሙት ንግግር “የእምነት ሰማዕትነት ያበቃለት ጉዳይ መስሎ ነው የሚታየው፣ ቢሆንም ቅሉ ባለንበት ዘመን በተለያዩ መንግሥታት በሚከተሉት ሥርዓትና ውሳኔ መሠረት የሚፈጸም፣ ጎልቶ የሚታይ ወቅታዊነት ያለው ተጨባጭ ነው” ሲሉ። “በተካሄደው ውይይት ጸረ ክርስትያን የሚፈጸመው አመጽ በማጋለጥ አመጹን ለመቋቋም እንደሚቻልም” ተጠቅሰዋል። የናፖሊ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ክረሸንዚዮ ሰፐ ለጉባኤው ባሰሙት ንግግር “ሰማዕታትን በጠቅላላ ሚሥጢረ ተክሊል አላፈርስም እምቢ የሚለው፣ ጽንስ አላስወርድም ለሞት ባህል እምቢ የሚሉት እናቶች ለወቅታዊው አሳሳች መሠረት ቢስ ባህል እምቢ የሚሉት ወጣቶች በመጥቀስ በጠቅላላ ክርስትናዊው ልክነቱን አለ ፍራት ዕለት በዕለት መኖር ለገዛ ራሱ ሰማዕትነት ነው፣ ዕለት በዕለት ለክፋት መንፈስ አልገዛም” ማለትም መሆኑ ጭምር አብራርተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.