2009-07-03 17:42:01

ቫቲካን የጋሊለዮ ጋሊለይ ሰነዶች ይፋ አድረገች፡


ቫቲካን የጋሊለዮ ጋሊለይ ሰነድ ይፋ አደረገች ፡ ሰነዱ ያቅረቡት በቅድስት መንበር የቫቲካ ምስጢራዊ ሰነዶች መዝገብ ቤት ዋና ሐላፊ ብፁዕ አቡነ ሰርጂዮ ፓጋኖ ናቸው።

ይህ በቫቲካን ክፍል ማኅተም ለውስጥ ለውጭ ጋዜጠኞች እና ለሳይንስ ጠበብት የተሰጠ ሰነድ፡ ነፍሰሄር ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እኤአ በ1992 ጋሊለዮ ጋሊለይን በተመለከተ የሰጡት መግለጫ ምርኩስ ያደረገ መሆኑ ተመልክተዋል።

በቫቲካን መዝገብ ቤት እኤአ ከ1877 እና 1910 መሀከል የተያዙ የጋሊለዮ ጋሊለይ አራት ዕትም ሰነዶች ታቅበው መኖራቸው ተገልጠዋል።

የጋሊለይ ጋሊለዮ ሰነዶች ሰማይ መሬት እና ህዋ ትኩረት የሰጡ መሆናቸው ብፁዕ አቡነ ሰርጂዮ ፓጋኖ አስገንዝበዋል።

በቫቲካን የምስጢራዊ ሰነዶች መዝገብ ቤት ዋና ሐላፊ ብፁዕ አቡነ ሰርጂዮ ፓጋኖ እንዳመለከቱት፡ በሰባት ሚእተኛ ዓመት ቤተክርስትያን የሳይንስ አዋቂ የጋሊለዮ ጽሑፎች እንዳይነበቡ መግታትዋ ጠቅሰው ጉዳዩ አሳዛኝ መኖሩ ጠቁመው ፡ የሳይንስ ምሁሩ ጽሑፎች ከ1741 ወዲህ መነበብ እና መታየት መጀመራቸው አስታውቀዋል።

የጋሊለዮ/ጋሊለይ ጉዳይ እምነት እና ቅዱሳን ጽሑፎች በተመለከተ ለቤተክርስትያን ትምህርት መስጠት ስህተት መሆኑ በሌላ በኩል ደግሞ ቤተክርስትያን ወደ ሳይንስ ጠጋ ማለት እንዳለባት የሚያስተምር እና ተሞክሮ ሰጪ መሆኑ ብፁዕ አቡነ ሰርጂዮ ፓጋኒ ገልጠዋል።

በቫቲካን የምስጢራዊ ሰነዶች መዝገብ ቤት ዋና ሐላፊ ብፁዕ አቡነ ፓጋኖ አያይዘው እንዳስረዱት በጋሊለዮ ጋሊለይ ግዜ ኡርባኖ ስምንተኛ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት መኖራቸው አስታውሰው ፡ ጋሊለዮ የሳይንስ ጥናቱ በንድፈ ሐሳብ መልክ ለቤተክርስትያን እንድያቀርብ መጠየቃቸው እና ጋሊለዮ ሐሳቡ ውድቅ በማድረግ ቤተክርስትያን የቅዱስ መጽሐፍ ይዘታ እና ትርጉም በተመለከተ ያላትን አቋም ዳግመ ጥናት ታደርግ ዘንዳ በመጠየቁ በሱ እና በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ኡርባኖ ስምንተኛ መሀከል የነበረውን ግንኙነት ወደ መሻከር ማለቱ ገልጸዋል ።

ይሁን እና ብፁዕ አቡነ ሰርጅዮ ፓጋኖ እንደገለጡት ፡ ከየሳይንስ ምሁሩ ሰነድ ለመረዳት እንደተቻለው ፡ እሱ ማለት ጋሊለዮ ጋሊለይ ካቶሊካዊ እምነቱ ይዞ ኖረዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.