2009-07-03 17:42:17

ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የጵጵስና ሹመት ሰጡ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በዕድሜ ገደብ ምክንያት የፍራስካቲ ሰበካ ሊቅ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ጁዜፐ ማታረሰ በሕገ ቀኖና መሠረት ኃላፊነታቸውን ለማስረከብ ያቀረቡትን ጥያቄ ተቀብለዋል። የሰበካው ሊቀ ጳጳስ እንዲሆኑ እ.ኤ.አ. በ1984 ዓ.ም. የተወለዱት በ 1972 ዓ.ም. የክህነት ማዕርግ የተቀበሉት ከ 1980 ዓ.ም. የካቶሊክ ትምህርተ ሃይማኖት በሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር መሥሪያ ቤቶች ተጠሪ በመሆን እያገለገሉ ያሉትን የበርጋሞ ሰበካ ወሉደ ክህነት አባል ብፁዕ አቡነ ራፋኤሎ ማርቲኔሊን ሾመዋል።

ብፁዕ አቡነ ራፋኤሎ ማርቲነሊ በዚህ የካቶሊክ ትምህርተ ሃይማኖት በሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ሥር የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ትምህርተ ክርስቶስ ለመዘጋጀት የተካሄደው ጥናት በማቀነባበር ኅላፊነት ማገልገላቸውና ከ1999 ዓ.ም. የር.ሊ.ጳ. የክብር ሊቀ ጳጳሳት ሆነው መሾማቸው የቅድስት መንበር የዜና ምንጭ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.