2009-07-01 18:15:12

ጳጳሳዊ ቤተ ጸሎት


በቫቲካን ሐዋርያዊ ሕንፃ የሚገኘው ለር.ሊ.ጳ. እና ለተለያዩ ጳጳሳዊ ምክር ቤቶችና ቅዱሳት ማኅበራት የሚመሩት ለብፁዓን ጳጳሳት ለአስተንትኖና ጸሎት የሚያገለግለው በቅዱስ ጳውሎስ የሚጠራው ቤተ ጸሎት ለአምስት ዓመት ሲታደስ መቆየቱ የሚዘከር ሲሆን፣እፊታችን ሓምሌ 4 ቀን 2009 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በሚመሩት ጸሎተ ሠርክ በይፋ እንደሚከፈት ከቅድስት መንበር የተላለፈልን ዜና ያመለክታል።
ይህ ቤተ ጸሎት ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ሶስተኛ ልዩ ፍላጎት መሠረት የተሠራ ሚካኤል አንጀሎ የሠራቸው የቅዱስ ጳውሎስ እምነት መቀበልና እና የቅዱስ ጴጥሮስ ሰማዕትነት የሚገልጡ ንድፎች ያለበት መሆኑም ተገልጠዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.