2009-07-01 18:11:52

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የሓዘን መግልጫ መልእክት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ትላንትና በቪያረጆ ከተማ ባቡር ጣቢያ ክልል በተከሰተው የባቡር ቃጠሎ አደጋ ሳቢያ የደረሰው የሞት እና የመቁሰል አደጋ ልባቸውን በኃዘን እንደነካው በመግለጥ ለሞቱት እግዚአብሔር በመንግሥቱ እንዲቀበላቸውና ለቆሰሉት ምሕረት ጸልየዋል። RealAudioMP3

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የኃዘን መግለጫ መልእክት የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ፊርማ የሰፈረበት የቴሌግራም መልእክት ለመንግሥትና ለቪያረጆ ከተማ መስተዳድር መተላለፉ ከቅድስት መንበር የተላለፈልን ዜና አስታውቀዋል።

በተከሰተው የባቡር ቃጠሎ አደጋ ሳቢያ 12 ሰዎች የሞት ሌሎች 36 ሰዎች የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ተገልጠዋል። የሉካ ሰበካ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኢታሎ ካስተላኒ አደጋው የተከሰተበት ክልል በመጎብኘት፣ ለሟቾች ቤተሰብ አጽናንተዋል። ብፁዕነታቸው ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ የክልሉ ካህናት፣ በተለይ ደግሞ አደጋው ከተከሰተበት ክልል 200 ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የቅዱስ አንጦኒዮስ ዘ ፍራንቸስካውያን ቍምስና ካህናት በመገኘት ለተጎዳው ህዝብ አገልግሎት ለሟች ቤተስብ ማጽናናታቸው እና ቤቱንና ንብረቱን ላጣው ህዝብ በተለያዩ ቍምስናዎች እያስተናገዱ ናቸው ብለዋል።

“በእኔ የሚያምን አይሞትም” የሚለውን ክርስቶሳዊ እውነት መሠረት ህዝብ ዕለታዊ ኑሮውን ያነብና ይኖር ዘንድ ዘለዓለማዊ ሕይወት የምታበሥረው ቤተ ክርስትያን ድጋፍና ትብብር በማቅረብ ሁሉም በደረሰው ሓዘን ልቡ የተነካ ቢሆንም ቅሉ፣ ሁሉም እምነቱን እንዲያበረታ ካህናቱ ቀርበው በማጽናናት የሕይወት ትርጉም ክርስቶስ መሆኑ መስክረዋል። ስለዚህም በእግዚአብሔር አምሳያና አርአያ የተፈጠረው ሰው ከሚያጋጥመው አደጋ ባሻገር ክርስቶሳዊ ተስፋ የለበሰ መሆኑ በመረዳት ሕይወት በሞት እንደማይቀጭ መመስከር አለብን፣ ቤተ ክርስትያንም ይኸንን እውነት በማንገብ ባደጋው ሳቢያ ለተጎዳው ሕዝብ በማጽናናት አስፈላጊ እርዳታ እያቀረበች ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.