2009-07-01 18:13:23

ቅዱስ አባታችን በኩወይት የቅድስት መንበር ኅየንተ አማካኝነት የሓዘን መገልጫ መልእክት አስተላለፉ


153 ሰዎችን በማሳፈር ወደ ኮሞሮስ ደሴቶች ያቀናችው የየመን የሕዝብ አይሮፕላን በሕንድ ውቅያኖስ ወድቃ በመስመጧ የደረሰው የሰው ሕይወት አደጋ ምክንያት ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የቅድስት መንበር ዋና ፀሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶኔ የፈረሙበት የሐዘን መግለጫ ቴሌግራም በኩወይት ለቅድስት መንበር ተጠሪ ለብፁዕ አቡነ ሙንገድ ኤል ሓኪም መተላለፉ የቅድስት መንበር መግልጫ አስታወቀ። RealAudioMP3

ይን ንብረትነቱ የየመን አየር መንገድ የሆነው የህዝብ አይሮፕላን በኮሞሮስ ደሴት ርእሰ ከተማ ሞሮኒ ያቀና እንደነበርና እስካሁን በተደረገው ፍለጋ አንድ የአሥራ አራት ዓመት ፈረንሳዊት ልጅ ብቻ መትረፉዋም ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.