2009-07-01 18:16:00

መሃይምነትን በማጥፋት ክርስቶሳዊ እውነትን መመስከር


 ኦፓም በመባል የሚጠራው ከዓለማችን መሃይምነትን በማጥፋት ተልእኮ አገልግሎት የሚሰጠው እ.ኤ.አ. በ 2006 ዓ.ም. የተቋቋመው ብፁዓን ጳጳሳት ካህናት ገዳማውያን እና ዓለማውያን ምእመናን ያካተተው የወንድማማችነት ልኡካን በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ማኅበር በሚሰጠው አገልግሎት አማካኝነት የእግዚአብሔር ፍቅር የሚመሰክር መሆኑ የማኅበሩ ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ አልዶ ማርቲኒ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ያወጁት ዓመተ ካህናት ምክንያት በማድረግ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው። የእግዚአብሔር ልብ የሚመኛቸው ካህናት ያስፈልጉናል በማለት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የሰጡት ቃል በማስታወስም የሰው ዘር ደስታን ፍቅርን ይሻል አንዱ ካንዱ ሳይለይ ሁሉም የአንድ አባት ልጆች መሆናቸው በመመስከር የህዝቦች ችግር ለመቅረፍ መሃይምነትን ማስወገድ ከሚለው ተግባር በመነሳት፣ ከቤተ ክርስትያን ጋር እና በቤተክርስትያን በመመራት የእግዚአብሔር ፍቅር ለሁሉም ማብሠር የተሰኘው የማኅበሩ ዓላማ ዳግም የሚያነቃቃ ዓመት ነው ብለዋል።

ለካህናት ቅድስና እንዲጸለይ የካህን የመልካም እረኛ መሥካሪነት እና ጸላዪ ሕይወቱ እንዲጎላ የሚያነቃቃ ዓመት ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.