2009-06-29 17:33:10

ዓመተ ሐዋርያ ጳውሎስ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የመዝግያ ሥርዓት ተፈጸመ፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ትናትና ከቀትር በኃላ ከቅድስት መንበር ግድግዳዎች ውጭ በሚገኘው የቅዱስ ጳውሎስ ካተድራል ተገኝተው በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ምእመናን በተገኙበት የዓመተ ጳውሎስ መዝግያ ሥርዓተ ሰርክ መርተዋል። RealAudioMP3

የቁስጢንጢንያ ቤተክርስትያን ፓትርያርክ የብፁዕ ውቅዱስ ባርቶለመዮ አንደኛ ልዑካንም በዚሁ ሥርዓት መገኘታቸው ታውቆዋል።

በዚሁ ለአንድ ዓመት የዘለቀው ጳውሎሳዊ ዓመት ከተለያዩ ሀገራት ዓለም የመጡ ምእመናን ካተድራሉ መጐብኘታቸው ተገልጸዋል ።

ቅዱስ አባትቻን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ትናትና ከቀትር በኃላ የጳውሎሳዊ ዓመት መዝግያ ሥርዓት ሲፈጽሙ እንደገለጡት ፡ ካተድራሉ ውስጥ ለዘመናት በታቀበው መቃብር የተካሄደው የሳይንሳዊ ጥናት ግኝት የቅዱስ ጳውሎስ ቅሪት መሆኑ ያረጋገጠ ይመስላል ።

ቅሪቱ በመጀመርያ እና ሁለተኛ ከፍለ ዘመን የኖረ ሰው ቅሪት መሆኑ የሳያንስ ጥናት ግኝቱ ማረጋገጡ ቅዱስነታቸው አመልክተዋል።

ሐዋርያ ጳውሎስ አሁን ትረ ፎንታነ ቤተክርስትያን በሚገኝበት ተገሎ አሁን በስሙ በተሰየመው ጳጳሳዊ ካተደራል መቀበሩ ይታመናል ።

ካተድራል ቅዱስ ጳውሎስ ፡ በ1823 በእሳት እንደተቃጠለች የሚታወስ ሲሆን፡ ስትታደስ የ440 ዓመተ ምህረት ዕለት ያያዘ ጳውሎስ ሐዋርያ ሰማዕት የተጻፈበት እምነ በረድ መገኘቱ ሌላ መረጃ መሆኑም ተወስተዋል።

ካተድራሉ ውስጥ ከመንበረ ታቦ በታች የሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ሰማዕት ቅሪት ለማየት እንደሚቻል የሚታወቅ ነው።

ይሁን እና የካተድራሉ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አንድረአ ኮርደሮ ላንዛ ሞንተዘሞ እንደገለጡት ፡ ጳውሎሳዊ ዓመት ከመዘጋቱ በፊት ፡በተለይ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከተለያዩ የዓለም ሀገራት በብዙ ሺ የሚገመቱ ምእመናን ካተድራሉን ጐብኝተዋል።

ምእመናኑ ካቶሊካውያን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ክርስትያናዊ እምነት ተከታዮች ጭምር መሆናቸው ጠቅሰው ጳውሎሳዊ ዓመቱ ስኬታማ መኖሩ ብፁዕ ካርዲናል ሞንተዘሞሎ አስረድተዋል።

ቅዱሳን ጰጥሮሰ ጳውሎስ የመላ ክርስትያን እሴቶች መሆናቸውንም ብፅዕነታቸው በተጨማሪ ማስገንዘባቸው ተያይዞ ተነግረዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ በየቅዱስ ጳውሎስ ካተድራል አቅራብያ የቅድስት ተክላ መቃብር ለማሳደስ እየተካሄደ ባለው ስራ በእጅ የተሳለ የሐዋርያ ጳውሎስ ምስል መገኘቱ በቅድስት መንበር የቅዱሳን ቅርሶች አርከዎሎጂካዊ ማእከል ጳጳሳዊ ኮሚስዮን ከሰጠው መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል ።

ኢኮኑ ወይም አርማው ለብዙ ግዜ ከተጠና በኃላ የአራተኛ ክፍለ ዘመን ዕለት የሚታይበት ሆኖ የቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ አምሳል የሚያንጸባርቅ መሆኑ አለም አጠራጠር ለመናገር እንደሚቻል የኮኪስዮኑ መግለጫ አክሎ አመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.