2009-06-29 17:35:29

በዓለ ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስ ወጳውሎስ


የላቲን ሥርዓት በሚከተለው ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ዛሬ ዕለት የቅዱሳን ሐዋርያት የጴጥሮስና የጳውሎስ በዓል ተዘክሮ ተከብሮ የሚውልበት ቀን ነው።

ቅ.ኣ.ር.ሊ.ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ዛሬ ጥዋት ልክ ከዘጠኝ ሰዓት ተኩል ጀምረው፣ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በደማቅ ሥርዓት ያሸበረቀ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገዋል። RealAudioMP3

ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስና ጳውሎስ የሮማ ከተማ ጠባቂ ቅዱሳን እንደመሆናቸውም ዛሬ በከተማዋ ታላቅ በዓላቸው ነው።

ቅዱስነታቸው በቅዳሴው ሥርዓት ልሠላሳ አራት የመጥሮጶሊ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ አክሚም አልብሰዋል። አክሚሙ መጥሮጶሊው ሊቀ ጳጳስ ከሮማ ቤተ ክርስትያንና ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ያለው ግኑኝነት፣ በእነርሱ ሥልጣን ሥር መሆኑን የሚያመለክት ነው።

በዓለ ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስ ወጳውሎስ ክርስትያን በሁለቱ ሐዋርያት ታላቅነት እንዲያስተነትን አጋጣሚና ዕድል ይሰጡታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.