2009-06-29 17:38:09

ቅዱስ ጳውሎስ የካህን አርአያ ነው።


ቅ.ኣ.ር.ሊ.ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ትናንት በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ አደባባይ ላይ ከተሰበሰቡት ምእመና ጋር የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከመድገማቸው በፊት፤ ሁለት ሺኛው የቅዱስ ጳውሎስ ሓዋርያ የልደት መታሰቢያ ዓመት ሆኖ ስለከበረው ዓመትና ስለሰጣቸው ፍሬዎች ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው በዚሁ ትናንት እሁድ እኩለ ቀን ላይ ባስተላለፉት መንፈሳዊ መልእክት፣ ሓዋርያ አሕዛብ ቅዱስ ጳውሎስን አርአያነት ያለው ካህን ሲሉ ዓመተ ጳውሎስን ከዓመተ ካህናት ጋር በማዛመድና በማነጣጠር አትተዋል። RealAudioMP3

ቅዱስ አባታችን ዓመተ ጳውሎስትን በይፋ የዘጉት፣ በዓለ ቅዱሳን ሓዋርያት ጴጥሮስ ወጳውሎስ ምክንያት በማድረግ ትናንት ምሽት በቅዱስ ጳውሎስ ባዚሊካ ፍዎሪ ለሙራ በመሩት የጸሎተ ሠርክና ባሰሙት ሰፋ ያለ ስብከት ነበር።

ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ የቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ ዓመት በይፋ ለመዝጋት ወደ ተለያዩ አገራት ተወካዮች መላካቸው የሚዘከር ሲሆን፣ ወደ ቅድስት መሬት፣ መሊጦስ፣ ቆጵሮስ፣ ቱርክ፣ ግሪክ፣ ሶርያና ሊባኖስ የተላኩት ወኪሎች ዓመተ ሓዋርያ ጳውሎስን በደማቅ ሊጢርጊያውያን ከየቦታው የደረሱን ዜናዎች አመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.