2009-06-26 20:18:20

በሐምሌ ወር ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሚገናኝዋቸው የዓለም መሪዎች


እ.ኤ.አ በሐምሌ ወር 10 ቀን 2009 ዓ.ም. የተባበሩት መንግሥታት አመሪካ መሪ ፕረሲደንት ባራክ ኦባማ ቫቲካን እንደሚጐበኙ እና ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ጋር እንደሚገናኙ የቫቲካን ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ እና የፕረሲደንቱ ቃል አቀባይ ሮበርት ጊብስ አስታውቀዋል። የርእሰ ሊቃነ ጳጳስት እና የፕረሲደንት ባራክ ኦባማ ግንኙነት የመጀመርያ ግንኙነት መሆኑ የሚታወስ ነው።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በዚሁ ሐምለ ወር ላይ የጃፓን መንግሥት ፕረሲደንት ታሮ አሶ በግል ተቀብለው እንደሚያያነጋግሩ በዚሁ በተጠቀሰው ወር የአውስትራልያ መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ከቪን ሩድ እና የካናዳው አቻቸው ስተፍን ሃርፐር በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው እንደሚያነጋግሩ የቫቲካን ቃል አቀባይ ከሰጡት መግለጫ ለመረዳት ተችለውል።








All the contents on this site are copyrighted ©.