2009-06-26 20:01:23

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም እንዲሰፍን በድጋሜ አሳስበዋል፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ትናንትና ረፋድ ላይ በአኅጽሮተ ቃል ሮአኮ የሚጠራው የምስራቅ አብያተክርስትያናት ተራድኦ ማኅበር አባላት ተቀብለው ማነጋጋራቸው የቫዪካን መግለጫ አስታውቀዋል። RealAudioMP3

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በዚሁ ግኑኝነት እንደገለጹት የመካከለኛው ምስራቅ ሁኔታ በእጅጉ እንደምያሳስባቸው ጠቅሰው የቅድስት ሀገረ ጳለስጢና ቤተክርስትን ከእስራኤል ፍሊስጤም ግጭት የተሳሰረ መሆኑ ማመልከታቸው ተገልጠዋል።

የመካከለኛው ምስራቅ ታሪካዊ እና አሳዛኝ ግጭት መቀረፍ የሰላም እምነ መሠረት መሆኑ ያሰመሩበት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ፡ በአሁኑ ወቅት ጋዛ ሰርጥ ከሁሉም በመገለል ህዝብዋ ለችግር መጋለጡ አመልክተዋል።

የክርስትና እምነት መሬት ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት፡ያደገበት የተሞተበት፡ እና የተነሳበት ቦታ ቅዱሳን ቦታዎች ኢየሩሳሌም ቤተልሔም እና በአጠቃላይ መካከለኛው ምስራቅ ለረጂም ግዝያት ሰላም በመታጣቱ ሐዘን እንደሚሰማቸው ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ መግለጣቸው የቫትካን መግለጫ አስገንዝበዋል።

ባለፈው ቅርብ ግዜ በመካከለኛው ምስራቅ ያደረጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት አስታውሰው፡ ከካቶሊካዊ ማኅበረሰቡ ጋር መገናኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ አውስተው እ/ር ለዚሁ እንዲበቁ መፍቀዱ አመስግነው፡ በዚሁ አከባቢ ሰላም ይሰፍን ዘንዳ ዘወትር እንደሚጠልዩ መግለጣቸው መግለጫው አክሎ አመልክተዋል።

ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ከየመሃከለኛው ህዝብ ጐን በመቆም በዚሁ አከባቢ ያለውን ግጭት እንዲገታ የህዝቡ መሰረታውያን መብቶች ተከብረው ህዝቡ በሰላም እንዲኖር ትጸልያለች ለሰላም አበክራ ትጥራለች በማለት ቅዱስነታቸው ገልጠዋል።

ወደ ሮአኮ የምስራቅ አብያተክርስትያናት የተራድኦ ማኅበር በመመለስም መንፈሳዊ ማኅበሩ፡ በምስራቅ አብያተ ክርስትያናት ዙርያ ያሉትን ውሉደ ክህነትን ማንፈሳዊ እና ማተርያላዊ እገዛ እንዲሰጥ መማጸናቸው የቫቲካን መግለጫ አስገንዝበዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ፡ የእስራኤል ጸጥታ እንደተጠበቀ ሆኖ ማኅበረ/ሮአኮ ጳለስጢና ላይ ያለውን የስደተኞች እና የተፈናቀሉ ሕዝቦች ችግር ለመቅረፍ እንዲረባረብ መጠየቃቸውም ተነግረዋል።

በመጨረሻም ባለፈው ዓርብ የተጀመረውን እና ለአንድ ዓመት የሚዘልቀውን የካህናት ዓመት አስታውሰው የመላ ዓለም ካህናት ንጽህና እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ዘለቄታ እና ስኬታማነት ለመድኀኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ እና ለቅድስት ድንግል ማርያም ሰጥች ሰጥቻቸዋለሁኝ በማለት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ከሮአኮ ማኅበር አባላት መሰናበታቸው የቫቲካን መግለጫ አስታውቀዋል ።








All the contents on this site are copyrighted ©.