2009-06-25 12:37:29

ቅዱስ ኣባታችን በዓመተ ክህነት “ለወንድሞቼ ካህናት” በማለት ያቀረብዋቸው አስተንትኖዎች ለኅትመት በቁ


የቫቲካን ቤተ መጻሕፍት ማተሚያ ቤት ቅ.ኣ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለዓመተ ክህነት መክፈቻ በጻፉትና በሰበኩት መሠረት “አስተንትንዎች ስለ ክህነት” በሚል አርእስት ኣንድ ትንሽ መጽሓፍ አሳትመዋል። RealAudioMP3

የማተሚያ ቤቱ አስተዳዳሪ ኣባ ጁሰፐ ኮስታ “ምእመናን ከካህን የሚፈልጉት ኣንድና ብቸኛው ሃብት እግዚአብሔርን ብቻ ነው” የሚለውን የመጽሓፉ መክፈቻ የሆነውን የመጀመርያውን አስተንትኖ አመልክቶ ለቫቲካን ረድዮ በሰጠው መግለጫ፣ “ካህን የገዛ ራሱ ሳይሆን የኢየሱስ ነው፣ ለእግዚአብሔር የተገባ ሰው ነው፣ ስለዚህ ከክርስቶስ ተዋህዶ ኣንድ መሆን ኣለበት፣ ካልአ ክርስቶስ በመሆን እያንዳንዱ ሰው እስከሚድን ድረስ እንደክርስቶስ ያለውን ክብር በገዛ ፈቅዱ ትቶ አገልጋይ መሆንን መምረጥ አለበት፣ ይህም ካህን የክርስቶስ አዲስ ማንነት ለብሶ እንደገና ህይወቱን ማቀናጀት ኣለበት በገዛ ራሱ ፍቃድና አሳብ ሳይሆን በክርስቶስ አሳብና ፍቃድ መታደስ ያስፈልጋል፣ የክህነት ምርጫ የአንድን ሰው ሕይወት የሚለውጥ የጠለቀና ሥር ነቀል ምርጫ ነው፣” ብለዋል።

ኣባ ኮስታ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ካህንን እንደ የክርስቶስ ጓደኛ የሚገልጹትን ለማብራራት ተጠይቀው ሲመልሱም፣ “ይህ ጓደኝነት አብሮ መኖር ነው፣ ካህን ከክርስቶስ ጋር ያለውን ግኑኝነት ማጠንከር አለበት፣ የኢየሱስ ጓደኛ መሆን ማለት የቢታንያ ሕይወትን መኖር ነው፣ እንደ ቅዱስ ዮሓንስ ሓዋርያ ከኢየኡስ ልብ ለልብ መወያየት፣ በሕይወት ዘመኑ ኢየሱስን እጎኑ እንዳለ አምኖ መጓዝ፣ ለምታፈቅረው ጓደኛ ከምታሳየው ፍቅር በምንም መጕደል የለበትም፣ ከክርስቶስ ጋር የሚደረገው ጓደኛነት የሕይወት መሠረት ነው፣ ይህ ቀስ በቀስ ይለመዳል በመጨረሻም ልክ እንደ ክርስቶስ እስከ መሆን ከፍ ይላል” ብለዋል።

ቅዱስ ኣባታችን ከካህነ ክርስቶስ የሚጠበቀውን አበክረው ሲገልጡ ‘ከካህነ ክርስቶስ የምጣኔ ሃብት የፖሎቲካ ወይም የሌላ መስክ ዕውቀትና ሙያ ሳይሆን የመንፈሳዊ ሕይወት አመራር ወይም የሥነ መንፈሳዊነት ሊቅነት ይጠበቃል’ ያሉትን እንዲገልጹ ኣባ ኮስታን ጋዜጠኛችን ጠይቆአቸው ሲመልሱ፣ ‘ካህነ ክርስቶስ በመሠረቱ መንሻውን መዘንጋት የለበትም፣ ነገሮችን በክርስቶስ አመለካከት ማየት አለበት፣ አሳቡም የክርስቶስ የእግዚአብሔር መሆን አለበት፣ ካህነ ክርስቶስ በተልእኮው አንዳንድ አስፈላጊና መሠረታዊ የሆኑ የምጣኔ ሃብት ወይም የመዋቅር ነገሮች የሚያደርጋቸው በማይገኝበት ኣጋጣሚ የቻለውን ሲያበርክት ይታያል፣ እንዲህ ባለ ኣጋጣሚም ይሁን ካህን መንሻውን መርሳት የለበትም የክርስቶስ አመለካከት የክርስቶስ አሳብ ኖሮት ራሱን በገዛ ፈቃዱ ሌሎችን ለማገልግል ለማዳን እንደሰጠ ዘውትር ማስታወስ ኣለበት ሲሉ መልሰዋል።

ሌላው ነጥብ ‘ካህን ክርስቶስ ከሁሉም በላይ የጸሎት ሰው መሆን ኣለበት’ ብለው ቅዱስ ኣባታችን ኣደራ ያሉትን ኣባ ኮስታ ሲያብራሩ፣ ‘ጸሎት ለነፍስ እንደ እስትንፋስ ነው የካህን ነፍስም እንደሌሎች ይህ እስትንፋስ ያስፈልጋታል፣ የማይጸልይ ካህን የክርስቶስ ጓደኛ ሊሆን ኣይችልም፣ ከክርስቶስ ኣካል የሆኑ ምእመናንም በጓደኝነት ለመኖር ኣይችልም፣ ስለዚህ ጸሎት ለመኖር በሚያደርገው ትግል ብቻ ሳይሆን ለመንፈሳዊ ሕይወቱም መሠረታዊ ነው’ ካሉ በኋላ ለዓመተ ክህነት የሚያገለግል ሌላ መንፈሳዊ አስተንትኖ የያዘ መጽሓፍ የታተመ እንደሆነ ተጠይቀው ሲመልሱ፣ አዎ ኣባ ለዮናርዶ ሳፒየንዛ የደረሱት ‘በአርስ ቆሞስ በነበሩት በቅዱስ ዮሓንስ ማርያ ቫያነይ ፈለግ የካህን ሕይወት’ የሚል አርእስት የያዘ መጽሓፍ ዛሬ ታትመዋል

በቺታ ንዎቫ ማተሚያ ቤት ታተመዋል፣ ደራሲው አርእስተ ሊቃነ ጳጳስት ጳውሎስ 6ኛ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊና በነዲክቶስ 16ኛ ስለ ቅዱስ ያሉትንም በመጽሓፉ አካተዋል በማለት ቃለ መጠየቁን ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.