2009-06-25 12:39:05

ምሥራቃውያን ኣብያተ ክርስትያንን የሚረዱ ድርጅቶች ስብሰባ ተጠናቀቀ


በ(ROACO) ምሕጻረ ቃል የሚታወቀው ምሥራቃውያን ኣብያተ ክርስትያንን የሚረዱ ድርጅቶች ድርገት ለሦስት ቀናት ያካሄደው መንቃዊ ጉባኤ አጠናቀቀ። RealAudioMP3

ለምሥራቃውን ኣብያተ ክርስትያን የሚያስብ ማኅበር ሓላፊ ብፁዕ ካርዲናል ሳንድሪ በጉባኤው ባሰሙት ንግግር በቅድስት መሬት የሚገኙ ክርስትያን ጌታ በመካከላችን መመላለሱን በሕይወታቸው ይመሰክሩልናል ብለዋል።

በትናንትና ስብሰባ ድርገቱ የተወያየባቸው ነጥቦች፣ ቅ.ኣ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ዘንድሮ እአአ ከግንቦት 8 እስከ 15 ቀን በዮርዳኖስ እስራኤል እና ፍስልሥጤም ያደረጉትን ሓዋርያዊ ጉብኝት እና በቅድስት መሬት የሚገኙ ማኅበረ ክርስትያን ጉዳይ ነበሩ። የቅዱስነታቸው ሓዋርያዊ ጉብኝትን አስመልክተው ብፁዕ ካርዲናል ለዮናርዶ ሳንድሪ፣ ‘በቅድስት መሬት ቅዱስ ኣባታችን ያደረጉት ሓዋርያዊ ጉብኝትን ልዩ የሚያደርገው ከቦታዋ ቤተ ክርስያን ያደርጉት ግንኝት እና ለማኅበረ ክርስትያኑ ‘ቦታው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተመላለስበትን ሁሉ ስለሚተርክ እዛ ሕያው የሕንፃ ድንጋዮች በመሆን መስክሩ’ ብለው የተማጠኑት ነው፣ በማለት የዘንድሮው የሮኣኮ ለምሥራቃውያን ኣብያተ ክርስትያን የሚረዱ ድርጅቶች ድርገት የቅድስት መሬት ክርስትያኖችን ቅድምያ በመስጠት እንዲረድዋቸው አደራ ብለዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ሳንድሪ ከቫቲካን ረድዮ ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ስለ ስብሰባው እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል። “ድርገቱ በዘንድሮው ስብሰባው መርኃ ግብር ለቅድስት መሬትንና ቡልጋርያን ቅድምያ በመስጠት ይወያያል፣ ለየት ያለ ትኵረት የተሰጠ ቅዱስ ኣባታችን በቅድስት መሬት ባደረጉት ሓዋርያዊ ጉብኝት ያደርጓቸውን ንግግሮችና ይዘታቸውን ይመለከታል፣ የቅዱነታቸው ሓዋርያዊ ጉብኝት ቅድስት መሬትን ለመላው የዓለም ካቶሊኮችና ሌሎች ክርስትያን ጐልታ እንደምትታይ አድረጋት፣ እኛም በቃላቸው መሠረት ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን ለሆኑት በጌታ መሬት ለሚኖሩት ያለንን ቅርበትና አጋርነት እናሳድሳለን፣” ሲሉ አብራርተዋ።








All the contents on this site are copyrighted ©.