2009-06-23 18:33:41

ቤተ ክርስትያንን ቅዱሳን ካህናት ያስፈልግዋታል


ቅ.ኣ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16 በዓመተ ክህነት መክፈቻ ላይ ባሰሙት ስብከት የክርስቶስ አካል ለሆነችው ቤተ ክርስትያን እውነተኛ እረኞች ያልሆኑና የበጎች ሌቦች ከሆኑ የካህናቶችዋ ክፍል ኃጢኣት በላይ የሚያሳዝናትና የሚያሳቃያት ምንም የለም። የዓመተ ክህነቱ ርእሰ ጉዳይ የክርስቶስ ታማኝነት የካህናት ታምኝነት ነው፣ ይህም ክርስቶስ ለአባቱ እስከ ሞት ታማኝና ታዛዥ ሆኖ በመሥዋዕቱ ዓለምን እንደአዳነ ሁሉ ቤተ ክርስትያንም ምእመናንን የእግዚአብሔር ምሕረት ፍቅር ቀምሰው እስከመመሥከር የሚረድዋቸው እረኞች ቅዱሳን ካህናት ያስፈልግዋታል። ቅዱስነታቸው የካህናት ቅድስና ምእመናንን መምራትና ማገዝ ብቻ ሳይሆን እሳቸው ራሳቸው በመጀመርያ የመለኮታዊው ፍቅር ምሥክር መሆን እንዳለባቸው ለዚህም የቅዱስ ዮሓንስ ማርያ ቫያንይ አብነት በመከተል ልባቸው በመለኮታዊው ፍቅር ተቃጥሎ እንደ ቅዱሱ ክህነት የጥቀ ቅዱስ ልበ ኢየሱስ ፍቅር ነው፣ የምሥጢረ ክህነታችን ስጦታ በቀጥታ ከዚህ ልብ መፈልቁና ወደ እኛ መጕረፉን እንዴት ኣድረገን መዘንጋት እንችላለን? እኛ ካህናት በትሕትናና በሥልጣን የካህናተ እግዚአብሔር የሆነ ሕዝብን ማገልገል እንዳለብን እንዴት መርሣት እንችላለን? ጥሪአችን ለቤተ ክርስትያንና ለዓለም የማያጠያይቅ ተልእኮ ሆኖ ለክርስቶስ ሙሉ ታማኝነትና ከእርሱ ጋር የማያቋርጥ አንድነት እንዲኖረን ያስገድዳል። ማለት ኣለብን ሲሉ ገልጸዋል።

ይህንን እተግባር ላይ ለመዋልና የጌታ ወንጌል ሰባኪዎች ለመሆን ትክክለኛና ቀጣይ የንባበ መለኮትና የተግባረ ኖልዎ ትምህርት ጠንቅቆ ማጥናት ያስፈልጋል፣ ከሁሉ በላይ ግን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ልብ ለልብ የሚያገናኘን የፍቅር ዕውቀት ያስፈልገናል።







All the contents on this site are copyrighted ©.