2009-06-23 18:34:12

ለዓመተ ክህነት የሚያገለግል መንፈሳዊ አስተንትኖ የያዘ መጽሓፍ በቺታ ንዎቫ ማተሚያ ቤት ታተመ


ቺታ ንዎቫ የተባለ ማተሚያ ቤት ባለፉት ቀናት “አብ እኔን እንደሚያፈቅረኝ 365 አጫጭር መንፈሳዊ ስብከቶች ለዓመተ ክህነት” በሚል ርእስ መጽሓፍ ኣሳተመ። ድርሰቱ በአራት መዝገቦች የተካፋፈለ ሲሆን ይህ አንደኛ ሆኖ የካህን ማንነትን ይገልጻል። ሁለተኛው ክህነትን በተግባር መኖር ወይም መመስከር የሚለውን ርእስ ይዘረዝራል። ሦስተኛ በክህነት ሕይወት ውስጥ የሚገጥሙትን ፈተናዎችና እክሎችን ይመልከታል። አራተኛውና የመጨረሻው ደግሞ ከክህነት የሚጠበቅ ተስፋን ይገልጻል። መጽሓፉ ለእያንዳንዱ የዓመተ ክህነት ቀን የሚሆን መንፈሳዊ ኣስተንትኖ የያዘ ነው።

መጽሓፉን ካሳተሙ አንዱ የሆኑትና የካህናት እንቅስቃሴ ሓላፊና የካቶሊክ ትምህርት ማኅበር ኣማካሪ ለሆኑት ኣባ ሁበርቱስ ብላውማይዘር የቫቲካን ረድዮ ጋዜጠኛ የመጽሓፉን ዓላማ እንዲገልጹ ጠይቆአቸው ሲመልሱ።

“ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16 ዓመተ ክህነትን በማወጅ ካህናት የሓዋርያትን ፈለግ በመከተል ኢየሱስ እንዳዘዘው ሕይወታቸውን እንዲያሳድሱ ጥሪ አቅርበዋል። መጽሓፉ ከዚህ ጥሪ የተወለደ ነው ለማለት ይቻላል። ዓላማውም ለካህናት የሚሆን መጽሓፍ በተለይ በዚህ በዓመተ ካህን ጠቅላላ ቤተ ክርስትያንን የሚመለከት ከመጽሓፍ ቅዱስ ከትምህርተ አበው ቅዱሳንን ጳጳሳት ከደረስዋቸው አስተንትኖዎች በተለይም ከቤተ ክርስትያን ጉብኤዎችና ከዘመናችን ምሥክሮች የተውጣጣ ጠለቅ ያለ ይዘት ያለውና መንፈስን የሚያሳድስ ሆኖ ዕለት ዕለት ከካህናት ጋር የሚጓዝ እንዲሆን የታቀደ ነው።” በማለት ገልጠዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.