2009-06-19 17:39:27

የክህነት ዓመት ዛሬ በይፋ ተጀመረ


ባለፉት ዝግጅቶታችን እንዳመለከትነው የካህናት ዓመት ዛሬ በጸሎተ ሠርክ ዘጥቀ ቅዱስ ልበ ኢየሱስ በይፋ ተጀመረ። ይህ እ.አ.አ ከዛሬ ሰኔ 19 ቀን ጀምሮ እስከሚመጣው ሰኔ 19 2010 ዓ.ም. የሚቆይ የጸሎት የአስተንትኖና የመታደስ ጊዜ በመሆን ካህናት ለዛሬው ዓለም ሕያው የወንጌል ምሥስክርነት እንዲሰጡ የሚቀሰቅስ ነው።

ለዚህ የክህነት ዓመት ማወጅ ምክንያት የሆነው በትሕትናው እና በቅድስናው የካህናት ኣብነት የቅዱስ ዮሓንስ ቫያነይ የዕረፍት 150ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ነው። የቅዱስ ዮሓንስ ቫያነይ ሕይወትና የክህነት ጥሪ ልክ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች በጻፈው ኣንደኛ መልእክቱ ምዕራፍ ኣንድ ላይ “እግዚአብሔር ጥበበኞችን ለማሳፈር በዓለም እንድ ሞኞች የሚቈጠሩትን ሰዎች መረጠ፣ ብርቱዎችንም ለማሳፈር በዓለም እንደ ደካሞች የሚቈጠሩትን መረጠ፣ በዓለም ሰዎች ዘንድ ክቡር ሆኖ የሚታየውን ነገር ለማጥፋት በዓለም የተዋረደና የተናቀ ከንቱም መስሎ የሚታየውን ነገር መረጠ።” እንደሚለው ነው። በጊዜው በነበሩት ሰዎች ሚዛን ቅዱስ ዮሓንስ ቫያነይ ለምንም ብቃት የሌለው ተብሎ የተገመተ ብዙ የተጋለ የእግዚአብሔር ሰው ነበር፣ ሆኖም ግን እግዚአብሔር መሣርያው እንዲሆን ስለመረጠው ለክህነት አዲስ ትርጉም ሰጠው፣ ክህነት የጥቀ ቅዱስ ልበ ኢየሱስ ፍቅር ነው በማለት ሌት ተቀን በቅዱስ ቍርባን ፊት ተደፍቶ በመጸለይ በአብነቱ ብዙ ሰዎች ወደ ጌታ እንዳቀረበና ከጊዜው ከነበሩ ካህናት የበለጠ እረኛ ከመሆን አልፎ የዓለም ሙሉ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ቆሞሶች ጠበቃ ሆነዋል።

የዛሬ ዕለት የጥቀ ቅዱስ ልበ ኢየሱስ ዕለት ነው፣ በዚሁ ዕለት መላዋ ቤተ ክርስትያን ስለ ካህናት ቅድስና ትጸልያለች። ቅ.ኣ. ለክህነት ዓመት መክፈቻ ለውድ በክህነት ወንድሞቼ ብለው በጻፉት መልእክት “ካህናት የሚያደርጉት ወደር የለሽ አገልግሎትና ሥጦታ ለቤተ ክርስትያን ብቻ ሳይሆን ለመላው የሰው ልጅ ዘር ነው፣ ካህናት በገሃድና ብሥውር የሚሰጡት ሓዋርያዊ አገልግሎት፣ ሕይወታቸውን አሳልፎ እስከ መስጠት የሚያበረክቱት የእግዚአብሔርና የጓደኛ ፍቅር አገልግሎት አስታውሳለሁ። በአንዳንድ አገሮች ለቤተ ክርስትያንና ለአገልጋዮችዋ ካህናት የሚያጋጥመውን ስደት እንዲሁም ዕንቅፋት ብምሬት አስታውሳለሁ’ ብለዋል።

ቅዱስነታቸው የመልእካታቸው መክፈቻ ያደረጉት የቅዱስ ዮሐንስ ቫያነይ ኣብነት ነው፣ ይህም እግዚአብሔር በነብዩ ኤርምያስ ምዕራፍ 3 ቍ 15 እንደ ልቤም የሚጠብቅዋችሁ እረኞች እሰጣችኋለሁ፥ በእውቀትና በማስተዋልም ይጠብቁአችኋል። ያለውን በማስታወስ ቅዱስ ዮሓንስ ቫያነይ እንደ እግዚአብሔር ልብ የሚጠብቅ እረኛ ነው። ከሁሉም በላይ እጅግ ትሑት ነበር፣ ይሁን እንጂ ካህን እንደመሆኑ መጠን ትልቁ የሰው ልጆች መልዕልተ ባህርያዊ የምሕረት ሥጦታ መሆኑም ያውቅ ነበር። ቅዱሱ የካህንን ማንነት በዚህ ምድር ብናውቅ ኖሮ በመደንገጥ ወይም በመገረም ሳይሆን በፍቅር በሞትን ነበር ይል ነበር፣ ተልእኮውን በደንብ የተረዳ ነበር፣ ከቅዱሱ የምንማረው ተልኮአችንን በደንብ ማወቅ፣ የእግዚአብሔር ጸጋ በብቃታችን የሚወሰን ባይሆንም በቅድስና የሚመራ የካህን ሕይወት ምኑን ያህል ለእግዚአብሔርና ለሰው ደስ እንደሚያሰኝና ብዙ ፍሬ እንደሚያፈራ መዘንጋት የለብንም። ለዚህም ነው ቅዱስ ዮሓንስ ቫያነይ ሕሙማንና ቤተ ሰቦችን በመጎበኘት ነግሦችን ጠለቅ ባለ መንፈሳውነት ለማክበር ቅድመ ዝግጅት በማካሄድ የተለያዩ የግብረ ሠናይ ተግባራት ለማካሄድ ግንዘብ እያጠርቀመ የሙት ልጆችን በመርዳት ትምህርት በማስተማርና ሌሎችን በዚህ ምግባረ ሠናይ በማሳተፍ መሠረታዊ አብነት አኑረዋል። ይህም አብነት በሁለትኛው የቫቲካን ጉባኤ የሚደገፍና ቆሞሶች ምእመናንን በሓዋርያዊ ግብረ ተልእኮ እንዲያሳትፉ ከምእመናን አብረው የካህናት ሕዝብ እንደሚያቆሙ መረዳት እንዳለባቸው ቅዱሱ ኣባታችን አደራ ብለዋል።

ቅዱስነታቸው የቅዱሱን ዕለታዊ ምሥክርነት በማስታወስ በተለይም በመንበረ ታቦት ተደፍቶ እቅዱስ ቍርባን ፊት መጸለይ፣ ዕለታዊ ቅዳሴና ወቅታዊ ኑዛዜ ከካህን መነጠል የሌለባቸው መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ቅዱስ ዮሓንስ ቫያነይ የሁሉም ምንጭ ቅዳሴ መሆኑ በመገንዘብ የካህን የሕይወት ምንጭ ቅዳሴ ነው ብለዋል። ለምሥጢረ ንስሓ የነበረው ጥልቅ እምነት ለማሳየት እርሱ ራሱ እስከ ሕይወቱ መጨረሻ ኑዛዜ በደምብ አዘውትረዋል ሌሎችን ማናዘዝም ዋና ትኵረት በመስጠት በመንበረ ኑዛዜ ብቀን እስከ 16 ሰዓት ይቀመጥ ነበር በዚህም ተግባር የብዙዎች ልብና ሕይወት መለወጥ ችለዋል። የጌታ የምሕረት ፍቅር እንደሚለውጥ ስላመነነ ስለሠራበት የአርስ ከተማ በጊዜው ትልቅ የነፍሳት ሆስፒታል ሆና ነበር።

ቅዱሱ ኣባታችን መልእክታቸውን ወደ አሁኑ ካህናት በማቅናት አዲሱን ቄንጠኛን ሕይወታችን በደንብ ለመኖር የቅዱስ ዮሓንስ ቫያነይ አብነት በመከተል የክርስትያን ቅድስና ትክክለኛ መንገድ የሚመሩ ድኅነት ንጽሕና እና ተአዝዞን መከተል እንደሚያስፈልግ ኣብራርተዋል። ድኅነትን በተመለከት ቅዱስ ዮሓንስ ቫያነይ “ምሥጢሬ እጅግ ቀላል ነው፣ ምንም ሳያስቀሩ ሁሉንም መስጠት ነው” ይላል። ንጽሕናው በመንበረ ታቦት በቅዱስ ቍርባን ፊት ሲጸልይ ይንጸባረቅ ነበር። መታዘዝን በተመለከት እግዚአብሔርን ፍላጎቱን በማሙላት ከማገልግል የሚበልጥ የለም ይላል።

በመልእክታቸው ኣዝማምያም ቅዱሱ ኣባታችን፣ ‘‘ካህናት መንፈስ ቅዱስ የሚሰጠንን አዳዲስ እንቅስቃስዎችን ተቀብለን መቻል እንዳለብን እንዲሆም ካህናት እርስ በእርሳችን እንድንዋደድና የጠነከረ አንድነት እንድንሳይ፤ በዚህም ከስብከትና ከትምህርት ይልቅ በተግባር አብነትና ምሥክር እንሁን። እንደ ቅዱስ ዮሓንስ ቫያነይ ሁሉንም በእግዚአብሔር እጅ በመተው ለዛሬው ዓለም የተስፋ የምሕረትና የዕርቅ መልእክተኞች እንደምንሆን እርግጠና ነኝ’’ በማለት ተማጥነዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.