2009-06-19 20:06:02

ኮት ዲቭዋር


የኮት ዲቭዋር ሰማንያ ስምንተኛ ረኪበ ጳጳሳት በፑጎን መካሄዱ ከአቢጃን የደረሰ ዜና ያመልክታል። በዚች ምዕራባዊት አፍሪቃ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል ብፁዕ አቡነ አምብሮይሰ ማታ ጳጳሳቱ ለሀገሪቱ ሰላም እና ሀገሪቱ ውስጥ የሚካሄደው ብሔራዊ ምርጫ በመልካም ተጀምሮ በመልካም እንዲደመደም እንዲጸልዩ ማሳሰባቸው ተገልጸዋል።

የኃይል ርምጃ ሁሉ ተወግዶ ሀገሪቱ ውስጥ ብሔራዊ ዕርቅ እንዲነግስ እና ህዝቡ በሰላም እንዲኖር ጳጳሳቱ ሳይታክቱ መስራት እንዳለባቸው ሕዋርያዊ ልኡኩ በረኪበ ጳጳሳት ተገኝተው መግለጻቸው ተነግረዋል። ቤተክርስትያን ከሕዝብ ጐን በመሰለፍ የሰላም የፍትሕ እና ዕርቅ መሪ ትሆን ዘንዳ አያይዘው ገልጠዋል።

በቅርቡ ሀገሪቱ ውስጥ በቅርቡ ብሔራዊ ምርጫ እንዲከናወን በእቅድ መያዙ ተያይዞ የደረሰ ዜና አስታውሰዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.