2009-06-19 20:02:59

ናይጀርያ


በናይጀርያ ርእሰ ከተማ አቡጃ ላይ ሲካሄድ የሰነበተው ብሔራዊ የቅዱስ ወንጌል ተልእኮ ምክር ቤት፡ አጠቃላይ ጉባኤ መደምደሙ ከዚሁ ቦታ የመጣ ዜና አስታውቀዋል።

ከጉባኤው ፍጻሜ በኃላ ምክር ቤቱ ለፊደስ ዜና አገልግሎት የላከው መልእክት እንዳመለከተው፡ በአጥቃላይ የጥምቀት ምስጢር የተቀበለ ክርስትያን ሁሉ የቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ አሠር በመከተል የእግዚአብሔር ቃል ለመላ ዓለም ማዳረስ ይጠበቅበታል።

ቃለ እግዚአብሒር ለሰው ልጅ ከመጀመርያ እስከ መጨረሻ እንድሚያሻው ዕለታዊ ምግቡ መሆን እንዳለበት በናይጀርያ የቅዱስ ወንጌል ተልእኮ ብሔራዊ ምክር ቤት ያወጣው መግለጫ አስገንዝበዋል።

ቅዱስ ወንጌል ሰባኪዎች በሚገባ ተዘጋጅተው በተሀገራቱ ባህል እና ልምድ መሠረት፡ ዘወትር ቃለ እግዚአብሔርን ለክርስትያን ህዝብ ማሰማት እንደሚጥበቅባቸው ለፊደስ ዜና አገልግሎት የተላከ መልእክተ መግለጫ ያመልክታል።

የካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ቅዱስ ወንጌልም በዘመናውያን መገናኛ ብዙኀን ለተማሪዎች እና ባለ በጎ ፈቃድ ሰዎች መሰራጨት እንዳለብት የአቡጃ ብሔራዊ የቅዱስ ወንጌል ምክር ቤት ማሳሰቡ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል።

እንደ ካቶሊካውያን ክርስትያን መጠን የቅዱስ ወንጌል መመርያ ተከትለን መልካም አርአያ መሆን ይጠበቅብናል ያለው የቅዱስ ወንጌል ብሔራዊ የምክር ቤቱ ምክር ቤት መልእክት ፡ ናይጀርያ ውስጥ መጥፎ ተግባራትን እርምታ የመስጠት እና ጨለማውን የማብራት ግዴታ አለብን እንደሚል የዜና አገልግሎቱ አመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.