2009-06-19 17:49:41

ቅዱስ ዮሐንስ ማርያ ቨኒ የካህናት ጠባቂ ቅዱስ


ቅ.አ.ር.ሊ.ቃ.ጳጳሳት በነዲክቶስ 16 ዛሬ ዓርብ ምሽት በይፋ ስለጀመሩት የክህነት ዓመት እና አላማው ወደ ካህናት ሰፊ መልእክት መጻፋቸው የሚታወቅ ሲሆን ስለ መልእክቱ የካህናት ቅዱስ ማኅበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ማውሮ ፒያቸንሳ ለቫቲካን ረዲዮ የሚከተለውን መግለጫ አቅርበዋል።

ከሁሉም በፊት አስቀድሜ ካህናት ር.ሊ.ቃ.ጳጳሳት የጻፉዋትን መልእክት ልብ ብለው እንዲያነቡና እንዲያሰላስሉ አሳስባለሁ፣ መልእክቱ የክህነት ጸጋና ስጦታ ታላቅነት ይገልጣል፣ የክህነት ጥሪ የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ሊቀበላቸው ከሚችለው ጸጋዎችና ስጦታዎች እጅግ የላቀና የበለጠ ነው፣ ስለዚህ ስለ ክህነት በምናስተነትንበት ጊዜ ከዚህ ሐቅና እውነታ መነሳትና መጀመር ይበጃል።

ካህናት በክህነት ተልእኮአቸው የክህነት ጥሪ ተምሳሌት የሆነውን የካህናት ጠባቂ ቅዱስ የኩራቶ ዘአርስ (ፈረንሣይ) ካህን ቅዱስ ዮሓንስ ማርያ ቨኒ ሕይወት አርአያነት ማሰላሰልና መከተል ይገባቸዋል ሲሉ ር.ሊ.ቃ.ጳጳሳት ለክህነት ልዩ ዓመት በጻፉት መልእክት ለካህናት አደራ ብለዋል በማለት የካህናት ቅዱስ ማኅበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ማውሮ ፒያቸንሳ ለቫቲካን ረዲዮ ሰለ ክህነት ዓመት ያቀረቡትን መግለጫ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.