2009-06-19 19:43:07

ሶማልያ


የሶማልያ ህውከት እና ግጭት ባለበት እንደቀጠለ መሆኑ፡ ከሞቃዲሾ የሚደርሱ ዜናዎች ያመለክታሉ። በመካከለኛው ሶማልያ ባላድወይን በተባለ ቦታ በሚገኝ ሆቴል በአክራሪዎች ተፈጽመዋል በተባለ የሽግግር መንግሥቱ ተጸጥታ ሚኒስትር ኦማር ሀሺ ጨምሮ ሀያ አራት ሰዎች መገደላቸው ዜናዎቹ ገልጸዋል። ከትናንትና ወድያም በየሞቃዲሾ መስጊድ ላይ በተፈጸመው ጥቃት ሌሎች አሥር ሰዎች ሕይወታቸው እንዳጡ የሚታወስ ነው።

አልሻባብ የተባለ አክራሪ ቡድን እና በየሀገሪቱ የሽግግር መንግሥት መካከል እየተካሄደ ያለው ግጭት በሲቪል ህዝብ ላይ ከፍተኛ እልቂት እያደረሰ በንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ ተገልጠዋል።

ሶማልያ ውስጥ የሚገኙ በሶስት ሺ የሚገመቱ የአፍሪቃ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ወታደሮችም በተጠንቀቅ ላይ መሆናቸው ዜናዎቹ አስታውቀዋል።

ካለፈው ግንቦር ወር እስካሁን ድረስ ሶማልያ ውስጥ ቢያንስ 250 ሰላማውያን ሰዎች መገደላቸው ተያይዞ የደረሰ ዜና አስታውቀዋል።

ሶማልያ ላለፉት አሥራ ስምንት ዓመታት ማእከላዊ መንግሥት አልባ በመሆን የቆየች ሲሆን ሕዝብዋ ለረሃብ ለእርዛት እና ለስደት መጋለጡ እየተነገረ ነው። ሁለት መቶ ሺ የሀገሪቱ ሕዝብ መፈናቀሉም የሚታወቅ ጉዳይ ነው።

ባለፈው ቅርብ ግዜ እዚህ ጣልያን ሮማ ውስት የሠላሳ አምስት ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ያሳተፈ የሶማልያ አገሮች አቀፍ አገናኝ ቡድን ስብሰባ መካሄዱ የሚታወስ ነው።

በዚሁ ስብሰባ የተገኙ የሀገሪቱ የሽግግር መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ተገኝተው መኖራቸው እና የሀገራቸው ሁኔት አስከፊ መሆኑ ገልጸው ነበር። አገሮች አቀፍ ማኅበረሰብ ሶማልያ የአፍሪቃ አፍጋኒስታን ከመሆንዋ በፊት ለሽግግር መንግሥት ሁለንትናዊ ርዳታ እንዲያቀርብም ጠይቀው ነበር።

የሶማልያ መንግሥት ጠቃልይ ሚኒስትር ዓሊ ሻር ማርከ የሶማልያ ሕዝብ አክራሪዎችን እንዲዋጋ ማሳሰባቸውም አይዘነጋም። የሶማልያ ዜጎች ብሔራዊ ዕርቅ በማድረግ ሀገራቸው ከውድመት ለማዳን የሚታገሉበት ግዜ አሁን መሆኑ የሽግግር መንግሥት ባለስልጣን መጠየቃቸውም ይታወሳል።

አንድ ሃይማኖት ቋንቋ እና ባህል ያለው የሶማልያ ሕዝብ እርስ በእርሱ ሲፋጅ ማየት አሳዛኝ መሆኑ የሀገሪቱ ፕረሲደንት አሕመድ ሸሪፍ ትናንትና መግለጫ ሰጥተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.