2009-06-19 19:21:26

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አሥራ ስድስተኛ ተቀብለው ያነጋገርዋቸው ባለሥልጣን


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አሥራ ስድስተኛ ትናንትና ረፋድ ላይ የማልታ ረፓብሊ ገኦርግ አበላ ተቀብለው ማነጋገራቸው የቫቲካን መግለጫ አስታውቀዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ እና የሞልታ መንግሥት መሪ ፕረሲደንት ግኦርግ አበላ በቅድስት መንበር እና በማልታ መሀከል ያለውን ግኙኘት የገሀገሪቱ ቤተክርስትያን ሁኔታ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች በተለይ የመካከለኛው ምሥራቅ ሁኔታ በተመልከተ መወያየታቸው መግለጫው ገለጠዋል።

የማልታ መንግሥት መሪ ፕረሲደንት ግኦርግ አበላ፡ ከየቅድስት መንበር የውጭ ጉዳይ ዋና ሐላፊ ከሊቀጳጳሳ ብፁዕ አቡነ ዶመኒክ ማምበርቲ ጋር በመገናኘት በተመሳሳይ ሐሳብ ለሓሳብ መለዋወጣቸው መግለጫው አመልክተዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ እዚህ ቫቲካን ውስጥ ቪሲታ አድ ሊሚና ማለት ሐዋርያዊ ጉብኝት በማካሄድ ላይ የሚገኙ የቨንጹወላ ጳጳሳት ተቀብለው ማነጋገራቸው ከነሱ በኃላም፡ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ተቀብለው ማነጋገራቸው የቫቲካን መግለጫ አስገንዝበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.