2009-06-17 16:35:57

የአፍሪካ ሕፃናት እና ወጣት ቀን


እ.ኤ.አ. ሰኔ 16 ቀን 1976 ዓ.ም. በደቡብ አፍሪካ ስዌቶ ከተማ 10 ሺሕ የሚገመቱት የአገሪቱ ዜጎች የተስተካከለና ብቃት ያለው የትምህርት ዕድል ለሁሉም በሚል የፍትኅ ጥያቄ የተነሳሳውን ሰላማዊ ሰልፍ ለመበተን የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ ሳቢያ RealAudioMP3 የተገደሉት 152 ሕጻናት የከፈሉት መሥዋዕት የወለደው ትላትና ታስቦ መዋሉ ተገለጠ። ይህ የደቡብ አፍሪካ ሕፃናት ገጠመኝ የሁሉም የአፍሪካ ሕፃናት መብትና ፈቃድ መከበር ጥያቄ ያጎላ መሆኑም ይነገራል። ቀኑን ምክንያት በማድረግ እ.ኤ.አ. ከ1976 ዓ.ም. ጀምረው ከሉዋንዳ በስተሰሜን 400 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው በኔጋጄ ከተማ በሚገኘው ትምህርት ቤት አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙት የኢየሱስ ልጆች ደናግል ማኅበር፣ የክልሉን ሕፃናት እና ቤተሰቦቻቸውን ለመደገፍ የተለያዩ የትብብር እቅዶች መወጠናቸው የማኅበሩ አባል እናቴ አዳልበርታ አስታውቀዋል።

ይህ የደናግል ማኅበር የሕፃናት ማዕከል በማቋቋም የትምህርት የመዝናኛ የተለያዩ ለሕፃናት እድገት የሚበጁ የሰብአዊና መፍነሳዊ ሕንጸት የመሳሰሉትን መርኃ ግብሮች ያካተተ እያከናወኑ መሆናቸውም እናቴ አዳልበርታ በመግለጥ ከመቀበል መስጠት ደስታ እንደሚሰጥ የሚገልጠው ወንጌላዊው ትምህርት የቀሰሙበት ማዕከል መሆኑም አስረድተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.