2009-06-17 16:10:53

በሃማኖቶች መካከል የሚደረገው ግኑኝነት


በካቶሊክ እና በሂንዱ ሃይማኖት መካከል ለሚካሄደው ግኑኝነት አንድ አዲስ ምዕራፍ መከፈቱ ከተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር የሚካሄደውን ግኑኝነት የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ዣን ልዊ ቱራን በህንድ ሓዋርያዊ ጉብኝት ፈጽመው በተመለሱበት ወቅት ይፋ ማድረጋቸው ተገለጠ።

ብፁዕ ካርዲናል ቱራን በህንድ ኦሪሳ ክልል አክራሪያን የሂንዱ ሃይማኖት ምእመናን ጸረ ክርስትያን አመጽ ከማነሳሳታቸው ቀደም ብሎ እ.ኤ.አ. ባለፈው 2008 ዓ.ም. ሓዋርያዊ ጉብኝት አካሂደው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ የሂንዱ አክራሪያን ጸረ ክርስትያን አመጽ መሠረታዊው ምክንያት ለይቶ ለማወቅ ብፁዕ ካርዲናል ታውራን የሂንዱና የካቶሊክ ሃይማኖት ዓበይት መንፈሳዊ መሪዎች ጋር በመገናኘት ሀሳብ ለሀሳብ እንዲለዋወጡ ያቀረቡት ጥሪ እ.ኤ.አ. ባለፈው ሰኔ 12 ቀን 2009 ዓ.ም. በህንድ ቦምበይ ከተማ ዝግ በሆነ ጉባኤ እውን መሆኑ ተገልጠዋል። RealAudioMP3

ተካሂዶ ከነበረው ዝግ ስብሰባ የሂንዱ ሃምማኖት በጠቅላላ አቢያተ ክርስትያናትን ጠንቅቀው የማያውቁ ማለትም ካቶሊክ፣ ፕሮተስታንት፣ ጴንጠቆስጤ የማይለያዩ ሁሉም ክርስትያን በሚል መለያ የሚያውቁዋቸው ሲሆን፣ በህንድ የሚፈጽመው ሌላውን ሃይማኖቱን የማስቀየር ተልእኮ አዛማቾች ተጠያቂው በጠቅላላ ክርስትያኖች ናቸው በማለት የሚያምኑ መሆናቸው ቀርበው ለመረዳት ችለዋል። ስለዚህ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ምንነት መለያና ታሪክ በማስደገፍ መሠረታዊው ማብራሪያ ለሂንዱ ሃይማኖት ዓበይት መንፈሳዊ መሪዎችን እንዳቀረቡ ገልጠዋል።

የሂንዱ ሃይማኖት መሪዎች የካቶሊክ ቤተ ክርስያን ምንነት ለይተው ካወቁ ወዲህ ከካቶሊክ ሃይማኖት ጋር ምንም አይነት ጥላቻ እንደሌላቸው ይፋ ማድረጋቸው፣ ብፁዕ ካርዲናል ቱራን በመጥቀስ፣ ይህ ሀሳብ ግኑኝነቱ አንድ አዲስ ምዕራፍ እንዲከፈት አድርገዋል ብለዋል። ካቶሊክ ቤተ ክርስያን ሌላው ሃይማኖቱን እንዲቀይር አስገዳጅና በጥቅም የተሸኘ ዘመቻ እንደማታክሂድም ለስብሰባው ባሰሙት ንግግር ማብራራታቸው ገልጠዋል። በመጨረሻም የሃይማኖቶች ግኑኝነት መሠረት የሃይማኖት ማኅበራዊ ሰላም ነው፣ ለማኅበራዊው ሰላም መሠረት የሃይማኖቶች ጤናማው ግኑኝነት መሆኑ በተካሄደው ስብሰባ ሰፊ ማብራሪያ እንደሰጡበት ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄድት ቃለ ምልልስ ገልጠዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም በህንድ ሰላምን የማይሹ አክራሪያ የሂንዱ ሃይምኖት ምእመናንን ለመለየት እንዲቻል፣ በሂንዱና የህንድ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን መካከል የጋራው ግኑኝነት እየተካሄደ መሆኑ ሲገለጥ፣ የህንድ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ሁሉም ሃይማኖት ለመቀራረብ ለመተዋወቅና ለጋራ መከባበር ያቀደ የጋራ ውይይት እያከናወነች መሆኗ ብፁዕ ካርዲናል ኦስዋልድ ግራሲያስ እንዲሁም በህንድ የቅድስት መንበር ተጠሪ ብፁዕ አቡነ ሎፐስ ኵይንታ እና ስሪ ጃየንድራ ሳራዋቲ ስዋሚና የተገኙበት የተለያዩ የሂንዱ ሃይማኖት መንፈሳዊ መሪዎች ያሳተፉ ጉባኤ በሙምባይ ከተማ መከናወኑ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.