2009-06-15 15:40:40

ፍቅር “ይኖራል፣ በመኖሩም ነገሮችን ይለውጣል”


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ትናንት እሁድ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከመምራታቸው በፊት ዕለቱ በዛ ባሉት አገሮች ኮርፑስ ዶሚኒ በዓለ ቅዱስ ቍርባን ከብሮ የሚውልበት ቀን መሆኑን አስታውሰው መላው ዓለም በረሃብ በመሰቃየት ላይ ያሉትን በሚሊዮናት የሚገመቱ ሕዝቦች ጉዳይ መርሳት እንደሌለበት አሳሰቡ።
ቅዱስነታቸው በፊታችን ሰኔ ሃያ አራትና ሃያ ስድስት በኒዮርክ ስለ ምጣኔ ሃብትና ገንዘብ መቃወስ ችግር መፍትሔ ለመሻት ሊካሄድ ታቅዶ ያለውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጉባኤ ጠቅሰው የረሃቡ ክስተት ጉዳይ ጨርሶ ተቀባይነት የሌለው ምክንያት አልባ ክስተት መሆኑን አስጠነቅቀዋል። በመጨረሻም ምእመናን በፊታችን ዓርብ ስለ ሚጀመረው የክነት ዓመት እንዲጸልዩ ጠይቀዋል። RealAudioMP3








All the contents on this site are copyrighted ©.