2009-06-15 15:34:00

ዓለም አቀፍ የደም ልገሣ ቀን


ዓለም አቀፍ የደም ልገሣ ቀን ትላትና ታስቦ መዋሉ ተገለጠ። የኢጣሊያ ብሔራው የሥነ ደም ማእከል ዋና አስተዳዳሪ የሕክምና ሊቅ ጁሊያኖ ግራዚኒ ዕለቱን ምክንያት በማድረግ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ RealAudioMP3 “በደም ልገሣ አስተዋጽዖ በመላ ዓለም 80 ሚሊዮን ከነዚህም ውስጥ 12 ሚሊዮን የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት ዜጎች እንደሚሳተፉ ጠቅሰው፣ በነዚህ የሚለገሠው ደም 38 በመቶ በማደግ ላይ ላሉት አገሮች የሚውል ሲሆን፣ የተቀረው ከጠቅላላው የዓለም ሕዝብ ብዛት ውስጥ 18% ለሚሽፍነው ለበለጸገው ያለማችን ሕዝብ የሚውል መሆኑ ገልጠው፣ የዚህ ምክንያት ደግሞ በማደግ ላይ ባሉት አገሮች የደም ልገሣና ቅስቀሳው ደካማ መሆኑ የሚያሳይ ነው ብለዋል።

800 ሚሊዮን ሕዝብ የሚኖርበት የአፍሪካ ደቡባዊው ሰሃራው ክልል ያለው የደም ባንክ ቤት እጅግ ድኻ መሆኑ ገልጠው፣ በ 79 አገሮች የደም ልገሣ ልምድ እምብዛም እንዳልሆነ እና ከ 1 ሺሕ ውስጥ ባመት አሥሩ ብቻ ደም እንደሚለግሥ አብራርተው፣ እ.አ.አ. ሰኔ 14 ቀን 1930 ዓ.ም. የደም ዓይነት ለይቶ ያወቁት የሳይንስ ሊቅ ካርል ላንደስታይነር መሆናቸው ሲነገር፣ እርሱ በተወለደበት ዕለት የዓለም አቀፍ የደም ልገሣ ቀን ተብሎ እንዲታሰብ አለ ምክንያት አይደለም ብለዋል። ስለዚሁ ዓለም አቀፍ የደም ልገሣ ቀን በበለጠ ለመረዳት ዳብሊው ዳብሊው ዳብሊው ነጥብ ዳብሊው ዲ ዲ ዲ ነጥብ ኮም የሚል ድረ ገጽ ለመጎብኝት ይቻላል።








All the contents on this site are copyrighted ©.