2009-06-15 15:36:10

ኮንጎ፣ የካሪታስ ማኅበር


በኮንጎ በካሪታስ የሚጠራው የካቶሊክ የተራድዖ ማኅበር ቅርንጫፍ የሕዝባዊ ግኑኝነት ጉዳይ ተጠሪ ጉይ ማሪን ካማንድጂ RealAudioMP3 “በዚህች አገር አማጽያን ሃይሎች በሚፈጽሙት ጥቃት ሳቢያ ያገሪቱ የገጠሩ ክልል በሰብአዊ ጉዳይ እጅግ እየተጎዳ ለነዋሪው ሕዝብም ሆነ እርዳታ ለሚያቀርቡ ማኅበርት በጠቅላላ ለደህንነት አሥጊ ነው” እንዳሉ ሚስና የዜና አገልግሎት አስታወቀ። ካማንድጂ የሰጡት መገልጫ የኡጋንዳ የኮንጎና የመካከለኛይቱ ሬፓብሊክ አፍሪካ የመከላከያ ሃይል ጠቅላይ አዛዦች በኪሳንጋኒ ባካሄዱት ጉባኤ የኮንጎ የመከላከያ ሃይል ቃል አቀባይ ለኦኔ ካሳንጋ በኮንጎ ምስራቃዊ ክልል ጣልቃ በመግባት የሚያውከው የጌታ ሠራዊት ተብሎ የሚጠራው ኃይል ቅስሙ እየተሰበረ ሱዳን መካከለኛይቱ ሬፓብሊክ አፍሪካናንና ኮንጎን በሚያዋስን ክልል ተወስኖ በመደናበር ላይ ነው ሲሉ ለሰጡት መግለጫ የሚጻረር መሆኑ ለመረዳት አያዳግትም፣ ሆኖም ያማጽያኑ ኃይል አባላት በተናንሽ ቡድን በመከፋፈል ጸጥታንና ደህንነትን እንደሚያውክና እ.ኤ.አ. በ 2008 ዓ.ም. የተለያዩ ጥቃቶችን በመሰንዘር 130 ሺሕ የሚገመት ህዝብ ለመፈናቀል አደጋና በብዙ ሺሕ የሚገመቱት ለሞት አደጋ ማጋለጣቸው ሚስና የዜና አገልግሎት በማስታወስ ገልጦታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.