2009-06-15 15:27:47

መንፈሳዊ የእግር ጉዞ


ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በኢጣሊያ ከማቸራታ ከተማ እስከ ሎረቶ በሚካሄደው 31ኛው መንፈሳዊ የእግር ጉዞ ተሳታፊያን ለሆኑት ምእመናንን ሰላምታና ቡራኬ አስተላልፈዋል። ይህ በያመቱ በኮሙኒዮኔ ኤ ሊበራዚዮነ ውኅደትና ነጻነት በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ማኅበር አማካኝነት የሚዘጋጀጅ ሲሆን የዘንድሮው መንፈሳዊው የእግር ጉዞ “ተስፋችንን በህያው እግዚአብሔር ላይ አኑረናል” በሚለው በቅዱስ ጳውሎስ ቃል መሪ ተሸኝቶ ባለፈው ቅዳሜ ልክ ከምሽቱ የናፖሊ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ክረሸንዚዮ ሰፐ በላ’አኲላ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ጁዜፐ ሞሊናሪ ታጅበው ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ተጀምሮ ወደ እሁድ በሚያሸጋግረው ሌሊት መከናወኑ ተገልጠዋል። RealAudioMP3

ይህ መንፈሳዊው የእግር ጉዞ ዕለታዊው ሕይወት ከእምነት ጋር ለማቆራኘት ዓልሞ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የምሥራች የሰው ልጅ ተስፋ እና የደስታ ምንጭ መሆኑ “እኔ ሕይወት እንድሆናቸውና እንዲበዛላቸውም መጣሁ” በዮሓንስ ወንጌል ምዕራፍ 10 ቍጥር 10 ያለውን የኢየሱስ ክርስቶስ ቃል መሠረት በማድረግ የዛሬ 31 ዓመት በፊት የተጀመረ መሆኑ” በኢጣሊያ የፋብሪያኖ ማተሊካ ሰበካ ጳጳስ ብፁዕ ኣቡነ ጃንካርሎ ቨቸሪካ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሂዱት ቃለ ምልልስ አብራርተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም ባለፈው ረቡዕ ር.ሊ.ጳ. እግዚአብሔር አብሮአቸው ስለሚጓዝ ወጣቱ ትውልድ ተስፋ ያለ መቁረጥ ብርታት ይኖራቸው ዘንድ አደራ ማለታቸውና ይኽን መልእክት በመንፈሳዊው የእግር ጉዞ ለሚሳተፉት ወጣቶች እንዲተላለፍ ያቀርቡት ጥሪ ይኽ የግር ጉዞ የወጠኑት የፋብሪያኖ ማተሊቻ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ኣቡነ ጃንካርሎ ቨቸሪካ የመንፈሳዊው የእግር ጉዞ የሰላም ችቦ በሎሬቶ እንዲበራ በተደረገበት እለት ይፋ ማድረጋቸው ተገልጠዋል። ቅዱስነታቸው ትላትና በዚህ የመንፈሳዊው የእግር ጉዞ ለተሳተፉት ሁሉ ቡራኬ ማቅረባቸው ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.