2009-06-12 18:04:51

ፕረሲዳንታዊ ብሔራዊ ምርጫ በኢራን፡


ዛሬ በኢስላም ረፓብሊክ ኢራን ውስጥ ፕረሲዳንታዊ ብሔራዊ ምርጫ እየተካሄደ መሆኑ ከርእሰ ከተማ ተህራን የደረሰ ዜና አስታውቀዋል። የዚሁ ብሔራዊ የፖሊቲካ ውድድር ከፍተኛ ተወዳዳሪዎች ለሁለተኛ ግዜ በመወዳደር ላይ ያሉ አሕመዲነጃድ እና የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙሳቪ መሆናቸው ተነግረዋል። ፕረስደንት አሕመዲነጃድን በመወዳደር ላይ ያሉ ሙሳቪ ዘመናዊ ወግ አጥባቂ መሆናቸው የሃገሪቱ መገናኛ ብዙኀን ያመለክታሉ።

ከተህራን የደረሰ ዜና እንዳመለከተው፡ የቀድሞ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ራፍሳንጃኒ እና የኢራን የሃይማኖት የበላይ መሪ አያቶላህ ካመነይ ተገናኝተው የፕረሲደንታዊ ምርጫ ሂደት እና ጥራት በተመለከተ ሐሳብ ለሐሳብ መለዋወጣቸው ተገልጠዋል።

የወቅቱ የኢራን መሪ የፕረሲደንት አሕመዲነጃድ ተወዳዳሪ ሙሳቪ በየምርጫ ዘመቻ ግዜ ፕረሲደንት አሕመዲነጃድ በሚከተሉት የተሳሳተ ፖሊሲ ኢራን ከዓለም መድረህ ነጥለዋል በማለት መተቸታቸው ከተህራን የደረሰ ዚና አስገንዝበዋል ።

በሙሳቪ አመለካከት፤ የፕረሲደንት አህመዲነጃድ ጸረ ዩናይትድ ስቴይትስ እና እስራኤል የሚከትሉት ፖሊሲ ኢራንን ጐድተዋል እንጂ አልጠቀመም።

የኤኮኖሚ ፖሊስያቸውም ቢሆን ኢራንን ድሃ አገር እንድትሆን አድርገዋል በማለት መግለጫ መስጠታቸው የሚነገርላቸው ሙሳቪ ከተመረጡ ባለፉት አራት ዓመታት በአህመዲነጃድ መንግሥት የተፈጸሙትን ስህተቶች ለማስተካከል ቃል መግባታቸው ተመልክተዋል።

ይሁን እና አርባ ስድስት ሚልዮን ኢራናውያን ዛሬ ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት የኢስላም ረፓብሊክ ኢራን የሚመራ ፕረሲደንት እንዲለዩ ይጠበቃሉ።

ኢራን የኑክሌራዊ ጦር መሳርያ ባሌበት ከመሆን እንድትቆጠብ ከምዕራቡ ዓለም የቀረበላትን ጥያቄ ፕረሲዳንት አህመዲነጃድ ጉዳዩ ውድቅ ማድረጋቸው ተያይዞ የደረሰ ዜና አስታውሰዋል።

የኢራን መገናኛ ብዙኀን እንዳመለከቱት ከሆነ ሙሳቪ ካሸነፉ የኢስላም ረፓብሊክ ኢራን ከምዕራቡ ዓለም ያላትን አለመግባባት የመቅረፍ ከፍተኛ ዕድል አለ። አህመዲነጃድ እንደገና ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት ከተመረጡ ግን ሁኔታው ባለበት ቀጣይ እንደሚሆን ነው የሀገሪቱ የመገናኛ ብዙኀን የሚያመለክቱት።







All the contents on this site are copyrighted ©.