2009-06-12 18:18:13

የሊባኖስ ብፁዓን ጳጳሳት መገልጫ


በሊባኖስ የማሮናዊት ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ እ.ኤ.አ. ከግንቦት 31 ቀን እስከ ሰኔ 6 ቀን 2009 ዓ.ም. መካሄዱ የገለጠው ሲር የዜና አገልግሎት፣ RealAudioMP3 ይህ በየዓመቱ የሚካሄደው ጉባኤ ባወጣው የጋራ መገልጫ አንድነት የተረጋገጠባት ሊባኖስ ለመመሥረትና በአገሪቱ የሚታዩት ውጥረቶች ለማርገብ የሕዝብ ተሳታፊነት የሚረጋገጥበት ፖሊቲካዊ ሂደት ወሳኝ መሆኑ ተመልክቶ እንደሚገኝ ካሰራጨው የዜና ምንጭ ለመረዳት ተችለዋል።

የአገሪቱ መንግሥትና እንዲሁም ሕዝባዊው ሸንጐ የኤኮኖሚ መዋቅር፣ የትምህርት መመሪያ፣ የጤና ጥበቃና የግብር ክፍያ መመሪያ ለማደስ አበክሮ እዲሠራ ብፁዓን ጳጳሳት ባወጡት የጋራ መግለጫ ማሳሰባቸው ሲር የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል።

መንግሥት ወጣቱ የአገሪቱ እምቁ ኃይል እንዳይባክንና ቦዝኖ እንዳይቀር የሥራ እድል እየተፈጠረለት እራሱን በመርዳት አገሩን ይደግፍ ዘንድ እንዲሁም ቤተሰብ የጤናማው ኅብረተሰብ መሠረት መሆኑ በመረዳት ልዩ ትኵረት ይሰጥ ዘንድና የሰላም መሠረት ውይይትና የአገርና የሕዝብ ጥቅም ማስቀደም መሆኑ ብፁዓን ጳጳሳት በማብራራት አደራ ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.