2009-06-12 15:03:12

ዓለም አቀፍ የንባበ መለኮት (ቲዮሎጊያ) ድርገት ሰነድ


ዓለም አቀፍ የንባበ መለኮት ድርገት፣ የሰውን ልጅ ባጋጣሚ ክስተቶች በሚገልጡት፣ እርሱም ከዘር ከጎሳ ከሃይማኖት እና ኃይል ያለው ከሚደነግገው ሕግ ባሻገር የሰውን ልጅ በጥልቀት እርሱነቱን በሚገልጡት እሰታዎች ላይ የተመሠረት ፖሊቲካ ኤኮኖሚ፣ የሰው ልጅ መብትና ፈቃድ ማኅበራዊው ሕይወት የሚመራ ኵላዊነት ሥነ ምግባር ለዓለማችን ከምን ግዜም በበለጠ እጅግ አስፈላጊ መሆኑ ባወጣው ሰነድ አመልክቶታል። RealAudioMP3

ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰኘው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ በዛሬ ኅትመቱ በዶሚኒካውያን ማኅበር አባል ፈረንሳዊ ፕሮፈሶር ኣባ ቶማስ ቦኒኖ በኵል የቀረበው የዚሁ የዓለም አቀፍ የንባበ መለኮት ድርገት ሰነድ፣ “ያለንበት ወቅት እሴቶችና ግብረ ገብ ነክ ጉዳዮች በተመለከተ ብዙ የሚባልበት ሆኖ እያለ ነገር ግን በማኅበራዊ ፖለቲካ ጉዳይ ፈጽሞ የማይገለጥ እንዲያውም በዚሁ ረገድ መንግሥታት የፖለቲካ አካላት ማኅበረ ሰብ ጭምር ለራሳቸው በሚያመች ረገድ እሰይታዎችንና የግብረ ገብ ነክ ጉዳዮች እያጠማዘዙ በመቆጣጠር እሰይታንና ግብረ ገብን የሚጻረር ሕይወት በመኖር እንደሚመሩ በማስመልከት፣ ግብረ ገብና ማኅበራዊ ፖለቲካ ጉዳይ የማይነጣጠሉ መሆናቸው” ያብራራል።

ኣባ ቦኒኖ አክለውም “ይህ ዓለም አቀፍ የንባበ መለኮት (ቲዮሎጊያ) ድርገት ምንም’ኳ የሰው ልጅ የሚደነግጋቸው ሕጎች ፍጹም ባይሆኑም ቅሉ አለ ምንም አድልዎና ልዩነት የሰውን ልጅ ሰብአዊነቱን ማዕከል ያደረገ ኵላዊነት ለበስ ሥነ ምግባር ገቢራዊ በማድረግ ብቻ ነው የሰው ልጅ መብትና ፈቃድ በማረጋገጥ ዋስትና መስጠት እንደሚቻል” የድርገቱ ሰነድ እንዳመለከተው ገልጠዋል።

“ዓለማዊነት ትሥሥር እጅግ ፈጣን በሆነ ሂደት አማካኝነት ወደ ፊት ሲል ይታያል፣ ነገር ግን ይህ ሂደት ሥነ ምግባር ካልታከለበት ጽናት አይኖረውም፣ ስለዚህ የኃይለኛው መብትና ፈቃድ የሚረጋገጥበት ዓለም ሳይሆን የሁሉም ክብር ለመጠበቅ ሥነ ምግባር ወሳኝ ነው። በሁሉም ባህሎችና ሃይማኖቶች ዘንድ የሚገለጥ አንድ የጋራ ሥነ ምግባራዊ ሃብት አለ፣ የክርስቶስ መምጣት መሠረታዊ ለውጥ ያበሠረት፣ ባህርያዊ ሕግ ለሚባለው አዲስና ጥልቅ ተሃድሶ አልብሶታል። ኢየሱስ ክርስቶስ የነበረው ቃል ሥጋ በመሆን በሰዎች ዘንድ ለባህርያዊው ሕግ የማይጻረር ከዚህ ጋር የሚስማማና ሙላት የሚሰጥ ሕያው ሕግ ሆኖ ተገኘ፣ ስለዚህ ባህራያዊ ሕግ አልተሻረም በፍቅር ሕግ መሠረት ሙላትን ሰጥቶታል” ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.